@ethiopian.electri: 📢የስማርት ኤስ.ቲ.ኤስ ቆጣሪ እና የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ጥበቃ📍 ✅የስማርት ኤስ.ቲ.ኤስ ቆጣሪ አሠራርና የኃይል አጠቃቀም ➡️ የተፈቀደ የኃይል መጠን ቁጥጥር:- የስማርት ኤስ.ቲ.ኤስ ቆጣሪዎች የሃይል አጠቃቀምን ይቆጣጠራሉ፣፣ 👉ገደብ ማለፍ ሲከሰት:-በርካታ እቃዎች በአንድ ጊዜ ሲሰካካ የኃይል አጠቃቀሙ ይጨምራል፤በዚያ ጊዜ ሜትሩ ይመልሳል፣ ✅የኃይል አጠቃቀምና የደንበኞች ኃላፊነት ➡️ክትትል ማድረግ:- ደንበኞች የኤሌክትሪክ ፍጆታቸውን በአግባቡ ማቀድና መቆጣጠር አለባቸው፣ 👉ኃይል ቆጣቢ እቃዎች መጠቀም :- የኃይል ብክነትን ለመቀነስ ኃይል ቆጣቢ የሆኑ እቃዎችን መጠቀም ያስፈልጋል ፣ ✅የኃይል ስርቆትና ጉዳቱ ➡️የስርቆት አሉታዊ ተጽእኖ:- የኃይል ስርቆት የኤሌክትሪክ ብክነትና መቆራረጥ ከማስከተሉ በተጨማሪ፣ በስርቆት የሚሳተፉ አምራች ድርጅቶች የገበያ ዋጋን ያዛባሉ፣ 👉ኮሚሽን:- የኃይል ስርቆት የሚፈጽምን አካል በመጠቆም ለሚተባበር አካል ከቅጣቱ ላይ 25 በመቶ ኮሚሽን/ክፍያ ይሰጣል፣ ✅የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ጥበቃ 👉የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ደህንነት:-የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ላይ የሚፈጸም ስርቆትና ጉዳት አለ፣ ➡️የህብረተሰቡ ተሳትፎ: ህብረተሰቡ መሰረተ ልማቶችን በጋራ ሊጠብቅና ጉዳት ሲደርስ ጥቆማ በመስጠት ሊተባበር ይገባል፣ #ኤሌክትሪክ #STSቆጣሪ #ኃይልቆጣቢነት #ግንዛቤ #EnergyEfficiency
Ethiopian Electric Utility
Region: ET
Saturday 28 November 2026 06:50:46 GMT
Music
Download
Comments
𝔪𝔲𝔞𝔷 :
አረ ለቆጣሪ ብር ከከፈልን ወር ሞላን እስካሁን አልመጣም ሚዲያ ላይ ምታወሩት ሌላ
2026-11-28 06:57:14
1
ወንዴ ፋሽን :
ከዛ በላይ መጠየቀ ይቻላል ወይ ስንጠይቅ አይፈቀድም ለምሳሌ 7.5 እጥፍ ብንፈልግ ምን ማድረግ አለብን
2026-11-28 14:25:25
0
wendye sleshi :
በዚህ ቆጣሪ የተነሳ ልናብድ ነው አንድ በሉ
2026-11-28 11:46:05
0
Reyan aymen :
እየበላን ነው
2026-11-28 13:06:29
0
husenahmed36 :
ሁልጊዜ የምታወሩት ስለ እራሳችሁ ጥቅም ብቻ ነው ማለት ይቻላል። እነዚህ ቆጣሪዎች ለተጠቃሚው የሚሰጠውን ጥቅምም በደንብ አብራሩልን።
ይህ ቆጣሪ አድስ በመሆኑ ተጠቃሚዎች በተደጋጋሚ ቅሪታዎችን ያቀርባሉ። ለምሳሌ አንድ ደንበኛ በአንድ ወር ውስጥ ተመሳሳይ kwh ከአንድ ጊዜ በላይ ቢሞላ የሚሞላበት ዋጋ ከመጀመሪያው በመቶ እና ከዚያ በላይ ፐርሰንት ይጨምራል። ለምሳሌ መጀመሪያ 40kwh ብገዛ የምከፍለው 170 ብር አካባቢ ነወ። በተመሳሳይ ይህንን ኪሎ ዋት መግዛት ብፈልግ መክፈል ያለብኝ ወደ 980 ብር አካባቢ ነው።
ይህ እንዲት ሊሆን ይችላል? በምን አግባብ?
ግልጽ ማብራሪያ ብታደርጉልን።
2026-11-28 12:47:46
0
To see more videos from user @ethiopian.electri, please go to the Tikwm
homepage.