@musictube369: ሙሉቀን መለሰ🥺💔 ''ምነው ከረፈደ'' መኪናን በዝግታ እያሽከረከሩ ለማድመጥ ምርጥ የሆነ ሙዚቃ እኮ ነው። 😏አዎ! መኪና የለኝም ግን ዋናው ቁምነገር እሱ አይደለም 😑 እኔ የምለው it's too late to say sorry! ኩረጃ መሆኑ ነው?🤧😂 -እስቲ ወደ ቁም ነገሩ እንመለስና በጣም እየናፈቀኝ ሙዚቃውን ደጋግሜ አደምጠዋለሁ። በተለይ "ምነው ከረፈደ" የሚለውን ... አላውቅም ብቻ የዚህ ሰው ውለታ አለብን ...🙌🥺 "በሚስጥር ቅበሪኝ" ን ሰምታችሁታል ግን ? ... "ዓይኔማ ወዳጅሽ" ንስ ... "እኔስ ተሳስቼ ወድጄሽ ነበረ " .... የሙሌ ሙዚቃዎች በድን አካልን መቀስቀስ የሚችሉ ፣ የጠወለገች ነፍስን የሚያለመልሙ ናቸው እኮ💙። አለም ላይ መተኪያ የሌላቸው አንድ አንድ ሰዎች አሉ።ከነሱ ውስጥ አንዱ ሙሉቀን መለሠ ነው ብዬ ለመናገር ቅንጣት አለመነታም። ሰንቶቻችን ከታክሲ መውረጃችንን አልፈን እንደሄድን ያለፍንበት ዘመን ይቁጠረው። ከ30 ዓመታት ባለይ ኑሮውን አሜሪካ ያደረገው ሙሉቀን መለሰ የሙዚቃውን ዓለም በመተው በመንፈሳዊ የሙዝሙር ሥራዎች ውስጥ ያሳልፍ እንደነበር ይታወሳል። ተወዳጁ ሙሉቀን መለሰ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የተቀረፀ የድምፅ ቃለ ምልልስም ሆነ የሙዚቃ ስራ ባይኖረዉም ሙዚቃ መጫወት ከጀመረበተ ከፈጣን ኦኬስትራ 1958 ጀምሮ እስከ1975 ዓ.ም የሰራቸውን በርካታ ተወዳጅ ስራዎቹን አበርክቶልናል:: ገና የ13 ታዳጊ ሳለ ነበር ሙዚቃን የጀመረው። በ1958 ዓ.ም በፈጣን ኦርኬስትራ ውስጥ ተቀላቅሎ በመግባት ለሁለት ዓመታት ያህል ሲያገለግል ከእዚያ በማስከተል በ1960 ዓ.ም ወደ ፖሊስ ኦርኬስትራ ክፍል በመግባት ይበልጥ በሙዚቃ ስራው ዝናን ማትረፍ ችሎም ነበር። በ1972 ዓ.ም ላይ ደግሞ ከዳህላክ ባንድ ጋር ተቀላቅሎ እስከ 1980ዎቹ ድረስ በነበሩት እጅግ ተወዳጅ የሙዚቃ ስራዎችን ሊያደርሰን ችሏል። ከ1980ዎቹ በኋላ ፊቱን ወደ መንፈሳዊ ሥራዎች በማዞር የመዝሙር ሥራዎችን ሲሠራ የቆየ ሲሆን እስከ ህልፈተ ሕይወቱ ድረስ በሀገረ አሜሪካ በእዚያው ቆይቷል። ሙሉቀን ሙዚቃ በቃኝ ብሎ ራሱን ከሙዚቃው ዓለም እስካገለለበት ጊዜ ድረስ በርካታ የሙዚቃ ሥራዎችን የሰራ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ጀግና ነው🙌። ሁሌም የሙሌ ሙዚቃዎቹ ከአፍ አይጠፉም "ባሳብ መዋለሌ , ቁመትሽሎጋ ነው ,አይኔማ ወዳጅሽ .....የቱ ተነስቶ የቱ ይተዋል በቆየበት አጭር የሙዚቃ ግዜ ዘመን የማይሽራቸው ስራዎችን አበርክቶልናል። ከዛም ባሻገር ድንቅ ሙዚቀኞችን በስራዎቹ ፈጥሮልናል 🙌🥺 ዛሬ እሱ ቢያልፍም ስራዎችህ ከመቃብር በላይ ህያው ሆነው ከዘመን ዘመን በከፋታ ይኖራሉ ነፍስህ ከደጋጎቹ ዘንድ ትረፍ ነፍስ ይማር🙏🙏 🗣ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን🙌🙏 @musictube 🇪🇹 #fyp #ሙሉቀንመለሰ #ምነውከረፈደ #musictube369 #ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🅼🆄🆂🅸🅲 🆃🆄🅱🅴
Region: ET
Thursday 14 August 2025 21:38:49 GMT
Music
Download
Comments
𝗚𝗘𝗭𝗜𝗦𝗛 ♐ መድፈኛው ⚪️🔴 :
የከዳችህ ሴት ሳትኖር የተከዳህ እንዲመስልህ የሚያደርግ ሙዚቃ 😭
2025-08-15 18:27:12
385
Abemelek 𝗧𝗬𝗚𝗔 :
1,ሰውነቷ 🔥
2,ምነው ከረፈደ 🔥
3,እኔስ ተሳስቼ ወድጄሽ ነበረ🔥
2025-08-18 12:47:43
162
Paብሎ Thoማስ Gaቪ :
እንዴት ከ 44 አመት በፊት እንደዚ ይቻላል እንዴ
2025-08-15 05:24:29
138
S A M :
የድሮ ዘፈን ፋርማሲ ነው መሸጥ ያለባቸው 🥰🥰
2025-08-15 18:30:09
108
Baelish :
This song +ጫት
2025-10-13 14:28:39
27
@aron_321 :
እየቃምክ ስማው ማይሰለች ሙዚቃ
2025-08-16 08:49:15
76
RESHIDWORKU🕸️🕸️ :
ከ41 አመት በፊት እንዴት ይኸን የመሰለ ግጥምና ዜማ ይሰራል ? 😳😳
2025-10-03 18:56:24
13
ድንቅ_ድንች :
በግዜው እንደነበሩ ሰዎች ብንሰማው ብላችሁ አስባችሁ ታውቃላችሁ?ልክ ፣ደዲስ እንደወጣ?
2025-08-15 14:33:35
59
user2436190500621 :
ያልተበደልሁትን በደል ሁሉ ነው የሚያስታውሰኝ
ሙሉቀን ማስተከዝ ይችልበታል🥰🥰🥰
2025-08-15 04:47:56
57
akiya :
ይህንን music ስሰማ ሳቤላ እሚለው መፅሀፍ ነው ትዝ እሚለኝ !የሚስተር ካርላይልና የሳቤላ ቤን የፍቅር ታሪክ በሙሉቀን የተዜመ ይመስላል !እሚገርመው መፅሀፋ በሬድዮ ተተርኮ ሲያበቃ የተለቀቀው ይህ ሙዚቃ ነበር!
2025-10-12 09:08:48
10
tarik Chelsea :
አዝማች እንደሌለው አቅ ነበር 🔥🔥🔥🔥🥰
2025-08-15 10:02:52
18
weitu :
ሙዚቃ ከእነ ሙሉ ክብሯ ምንይሰራል የእሷ ይቅርታ ብለህ ነው ሙሌ ረፈደ እኮ እግሬም ልቤም ሄደእኮ ታዲያ በትላንት የማይታለፍ ይቅርታ ባይኖርም ቅሉ እኔግን ቆርጫለው ለእኔም ለእሷ የሚበጀን መለያየቱ ነው አይመስልህም እሷም ዘግይታለች🙏.
2025-08-15 18:40:33
9
Nati Car Guy :
ዘፈን ልሸጥ ነው ፋርማሲ በር ላይ🥺🥺🥰
2025-08-19 14:52:46
6
Tsga Tsga :
በቃ ሙዚቃ ሲጋበዝ ከነሙሉ መረጃው ዋውው በጣም ደስ ይላል ሙልቀን ተአምረኛ ሙዚቀኛ ነው ሁሌም ስራዎቹ ሲታወሱ ዘመን ተሻጋሪ ሆነው ይደመጣሉ ነብሱን ይማረው
2025-08-16 03:50:39
18
AƁËĽ🕸 :
intro ❤️🔥❤️🔥😮💨
2025-08-15 05:59:10
20
ብሩክ :
😭😭😭😭😭 ብዙ ጊዜ የ ምወዳቸው ሰዎች ወይ ይሞታሉ ወይ ይከዱኝአል ግን ለምን ይሁን ክፉ ሰው አይደለሁም
2025-08-17 19:27:03
12
Nardos :
2025-08-17 11:44:40
6
betsi🧚♀️ :
real taste real music❤
2025-08-16 20:08:24
7
tade Oldies ♋ :
into 🔥🔥
2025-08-15 05:18:41
11
Kaliyor :
ሙዚቃ አፍ ቢኖረው ኖሮ እንደዚ ተዘፈንኩ😱 ይል ነበር 🥰
2025-08-17 19:55:23
6
ኢ.ና.ያ :
የሚያስተክስ ዘፈን 😭😭
2025-08-15 10:50:29
7
xxxx :
yehe muzika Abegaz 1989 be degami yezrw new brother
2025-08-21 15:29:39
5
Emu ye zeki & zakir እናት :
የ8 አመት በደል አስታውሼ ማልቀሴ😥 ግን ሁሉም አለፈ ፈጣሪ ይመስገን🙏🤲 የማያልፍ የሚመስል ሁሉ😥🙏❤
2026-02-11 16:43:39
3
To see more videos from user @musictube369, please go to the Tikwm
homepage.