@diaryofmahi: ይህን ከሃዲ እስካሳፍረው ድረስ ነፍሴን አትውሰዳት🙏 አባቱን ገና በልጅነቱ ቢሞትበትም ሌላ ክርስቲያናዊ መስፍን ወስዶ በጦር ኃይል አሰልጠኖ አሳድጎታል፡፡ የስሙ ትርጓሜ “ኮከብ ብሩህ፣ ፀሐይ” ማለት ነው፡፡ ፍልስጤም ውስጥ ልዩ ስሟ “ልዳ” በምትባል ቦታ በ277 ዓ.ም ጥር 20 ተወለደ ታላቁ ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ፡፡ ያሳደገው መስፍን ሲሞትም ኀዘኑን ጨርሶ ወደ ቤሩት ከተማ ሄደ፡፡ በዚያም የሚመለክና ሴት ልጆቻቸውን የሚገብሩለትን ደራጎን ገድሎ ሕዝቡን ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር መለሳቸው፡፡ የአባቱን ሹመት ለማግኘት ወደ ፋርስም ሲሔድ ንጉሱ ዱድያኖስ ከሰባ ነገሥታት ጋር ጣዖታት ሲያመልኩ ቢያገኛቸው በፊታቸው የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት መሰከረ፡፡ ሰማዕቱ ከመኳንንት ወገን መሆኑን የተረዳው ዱዲያኖስ አጵሎንን ብታመልክ እሾምሃለው አለው፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስም “አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስን ላንተ ሹመት ስል አልክደውም” አለው፡፡ ዱድያኖስም እጅግ ተቆጥቶ ብዙ አሠቃቂ መከራዎችን አደረሰበት፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስም ግን ጌታችንን “ይህን ከሃዲ እስካሳፍረው ድረስ ነፍሴን አትውሰዳት” በማለት ለመነው፡፡ እግዚአብሔርም ጽናትን ሰጥቶታል፡፡ የደረሱበት እጅግ አሠቃቂ መከራዎች የሰው ኅሊና ሊያስባቸው እንኳን የማይችላቸው ናቸው፡፡ በእንጨት ላይ ሰቅለው ሥጋውን በመቃን አስፈተተው፣ ረጃጅም ችንካሮች ያሉበት የብረት ጫማ አጫምተው ሂድ አሉት፡፡ ጌታችንም ቅዱስ ሚካኤልን ልኮለት ፈውሶታል፡፡ ሰውነቱን በመጋዝ አስተልትሎ ጨው ሲነሰንስበት ሥጋው መሬት ላይ ወደቀ፡፡ በሰባ ችንካሮች አስቸንክሮ፣ በእሳት አስተኩሶ፣ አናቱን በመዶሻ አስቀጥቅጦ፣ በሆዱ ላይ የደንጊያ ምሰሶ አሳስሮ እንዲያንከባልሉት አደረገ፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመንፈቀ ሌሊት በእጁ ዳስሶ ፈወሰው፤ ኃይልና ብርታትንም ሰጠው፡፡ በመከራው ብዛት ሦስት ጊዜ ሲሞት ጌታችን ሦስት ጊዜ ከሞት አስነሣው፡፡ ለሰባት ዓመታት ከተጋደለ በኋላም ሚያዝያ 23 በሰይፍ አንገቱን ተመቶ ሲሞት ሰባውን ነገስታት አጥፍቷቸዋል፡፡ ዓለምን የናቁ ገዳማውያን ይህን አብነት አድርገው ይጸናሉ በገድልም ይተጋሉ፡፡ #ተዋህዶ_ለዘላለም_ትኑር 🇪🇹💒 #ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ_መዝሙር_ተዋህዶ_ለዘለዓለም_ትኑር #ማርያም_እንወድሻለን #ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ_ፀንታ_ለዘለዓለም_ትኑር #ውበት_ነሽ_ለቤቴ_ድንግል_ማርያም_እመቤቴ

Diaryofmahi🇪🇹
Diaryofmahi🇪🇹
Open In TikTok:
Region: ET
Friday 01 May 2026 06:12:10 GMT
147
15
1
0

Music

Download

Comments

.21196318
@ነፃነት የፍቅር ሰዉ 2119 :
🙏🙏🙏
2026-06-15 04:30:28
0
To see more videos from user @diaryofmahi, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About