@ethiotimes5: መሀል አዲስ አበባ ላይ አንድ ድርቆሽ ፍርፍር 3500 ብር ! #maleda: የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ህንፃ 45ኛ ፎቅ ላይ የሚገኘውና በታዋቂው ኢትዮ አሜሪካዊ ሼፍ ባለቤትነት የሚተዳደረው Marcus Addis Restaurant አካባቢ አዲስ የወጣ ሰበር መረጃ አለ። እየተጠነቀቃችሁ..! 🤣 መጠነኛ የዋጋ ማሻሻያ አድርገዋል። በዚህ ሬስቶራንት የ 1 ድርቆሽ ፍርፍር ዋጋው 3,500 ብር ነው። ጣራ ላይ የምትጥሉት ድርቆሽ እዚህ 3,500 ብር ነው። ድርቆሽ ቀን ወጣላት..🤦♂️ . ሾርባ - 1,700 ብር ፣ እንቁላል ሳንዱች - 2,350 ብር ፣ ዋፍል በቺክን - 13,500 ብር ፣ ጥብስ - 9,500 ብር ፣ የፆም Vegan Grand - 8,500 ብር ነው። እንዲሁም ሌሎችም አሉ በዝርዝሩ ላይ። ምግብ ቤቱ 45ኛ ፎቅ ላይ ስለሆነ ነው መሰለኝ ዋጋውም አብሮት የተሰቀለው.. ። . ከሁሉም የገረመኝ ግን የቺክን ዋፍል ዋጋ ነው። ዶሮው ምናልባት ከመታረዱ በፊት Harvard ተምሮ የመጣ ዶሮ ሊሆን ይችላል። ዶሮው ከአናቱ ላይ ጣል ያደረገው ቆብ ዲግሪ የ University ዲግሪ ይሆናል 🐓 . ከሬስቶራንቱ Luxury Design እንዲሁም ምቾት ከዛ በተጨማሪ የሬስቶራንቱ ባለቤት አለም አቀፍ ሼፍ Marcus እንደመሆኑ መጠን ግን ይህንን ዋጋ Afford አድርገው በየእለቱ እየተመላለሱ የሚጠቀሙ በርካታ ደንበኞች አሉት። Marcus Samuelson አለም አቀፍ ዝና ያለው ሼፍ መሆኑ ይታወቃል። ሬስቶራንቱ በኢትዮጵያ ረጅሙ ህንፃ - 45ኛ ፎቅ ላይ መገኘቱ የሚሰጠው City View በራሱ ትልቅ ዋጋ አለው። ሙሉ ከተማዋን የሚያስቃኝ ገራሚ View አለው። . ታዲያ ይህ ዋጋ ከምግቡ ባሻገር ለሚገኘው ድባብና እይታ የሚከፈል ዋጋ ጭምር ነው። በነገራችን ላይ.. ለአንድ የውጭ ዜጋ ወይም ዲያስፖራ 3,500 ብር በአሁኑ ምንዛሬ ወደ 25 ዶላር አካባቢ ነው። ይህ ደግሞ በ New York ወይም London ለሚገኙ ከፍተኛ ደረጃ [ Fine Dining ] ሬስቶራንቶች ራሱ በጣም ተራ ዋጋ ነው። እዚህ እኛ ሀገር መሆኑ ነው እንጂ ትንሽ ያስደነገጠን ። # ፍራኦል ሀበሻ
🅴🆃🅷🅸🅾 🆃🅸🅼🅴🆂
Region: ET
Friday 01 May 2026 08:55:28 GMT
Music
Download
Comments
Negash Woderyelesh፡፡ኀቸ2 :
Hi how are you?
2026-05-04 19:11:31
0
Emutti 🇪🇹 🇺🇸🇺🇸 :
400 ጨምሬ እዚሁ ጎጃም 50 ኪሎ ጤፍ እገዛበታለሁ እንጂ
2026-05-01 17:36:02
4
user3013128493174አለ :
🥰🥰🥰🥰🥰
2026-05-01 18:22:33
0
To see more videos from user @ethiotimes5, please go to the Tikwm
homepage.