@_mono.wav: #capcut #yeunuoc

🪐
🪐
Open In TikTok:
Region: VN
Friday 01 May 2026 19:36:27 GMT
17069
40
0
5

Music

Download

Comments

There are no more comments for this video.
To see more videos from user @_mono.wav, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

📌 በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመን ዘንድ «የአርብ ውሃ» (ሳይናገሩና ሳይቀደሙ ማለዳ ከምንጭ የሚቀዳ ውሃ) ለዘመናት የኖረ ጥልቅ እና ውብ የቤት ውስጥ መንፈሳዊ ልማድ ነው። ✍️  እናቶች ይህንን ሥርዓት በታላቅ ጥንቃቄና እምነት የሚፈጽሙት ዝም ብለው ሳይሆን፤ ከመጽሐፍ ቅዱስና ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ጉዞ ጋር የተያያዘ ጥልቅ መንፈሳዊ ሚስጥር ስላለው ነው።    ✍️ ጉዳዮ ለምን «የአርብ ውሃ» ተባለ? መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረቱ ምንድን ነው?    💎1ኛ.  የዕለተ አርብ የውኃና የደም ሚስጥር (የፈውስ ምንጭ)፦  ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለተ አርብ በመስቀል ላይ በዋለ ጊዜ፤ ቅዱስ ሥጋው በጦር በተወጋ ቅጽበት ከመለኮታዊ ጎኑ «ደም ውኃ» ፈሰሰ (የዮሐንስ ወንጌል 19፥34)።.......ይህ ውኃ ለዓለም ሁሉ የኃጢአት መታጠቢያ፣ የበረከትና የፈውስ ምንጭ ሆኖ የተሰጠ ነው። እናቶች በአርብ ማለዳ ሳይናገሩ ውኃ ሲቀዱ፣ ያንን በዕለተ አርብ.... ከጌታ ጎን የፈሰሰውንና   ለዓለም ፈውስና ሕይወት የሆነውን መለኮታዊ ውኃ በምሳሌነት እያሰቡ በጽኑ እምነት ነው።    ✍️ 2ኛ. «ሳይናገሩና ሳይቀደሙ» የመሄዳቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሚስጥር......    እናቶች ውኃውን ለመቀዳት ጎህ  ሳይቀድ( ፀሐይ ሳትወጣ)  ሲነሱ፣ መንገድ ላይ ከሰው ጋር ላለመነጋገርና ላለመቀደም በጥንቃቄና በጭምትነት (በሱባዔ መንፈስ) ይጓዛሉ።...... ይህ ድርጊት ሁለት ታላላቅ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሚስጥራትን ይዟል....... ✍️3ኛ.  የክርስቶስን ዝምታና መከራ ማሰብ፦ ጌታችን በዕለተ አርብ ለፍርድ ሲቀርብና መከራ ሲቀበል እንደ በግ አፉን አልከፈተም፤ በዝምታ መከራን ታገሰ  (ትንቢተ ኢሳይያስ 53፥7).... ✍️  እናቶችም ይህንን የጌታን የጽሞናና የጭምትነት  መከራ በህሊናቸው እያሰቡ፣ በጸሎት ተወስጠው ስለሚሄዱ ከሰው ጋር ምድራዊ (ዓለማዊ) ወሬ አይነጋገሩም።    ✍️ 4ኛ. የማለዳው የሴቶች ጉዞ ምስጢር ፦ በትንሣኤው ዕለት ማለዳ ገና ጨለማ ሳለ፤ ቅዱሳት እናቶች (እናቶች) ሽቶና ቅባት ይዘው ወደ መቃብር የገሰገሱበት ሳይቀደሙና ከመንገድ ወሬ ርቀው በልባቸው  እያዘኑ ነበር (የሉቃስ ወንጌል 24፥1)።  ✍️ የአርብ ማለዳ የውኃ  ቅዳትም ይህንን ቅዱስ መንፈሳዊ ቅናትና ፍለጋ ያንጸባርቃል።    ✍️5ኛ.  ውኃው እንደ ጸበል ሆኖ የመፈወስ ኃይል፦ .....በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሔር በእምነት ለቀረበለት ነገር በግዑዛን ፍጥረታት ላይ ኃይሉንና በረከቱን ያሳርፋል።  💎 ለምሳሌ፦ የኤልሳዕ ጨው ውኃውን እንደፈወሰው (2ኛ ነገሥት 2፥21)... ወይም የጌታን ልብስ የዳሰሰችው ሴት በእምነቷ እንደዳነችው (የማቴዎስ ወንጌል 9፥22).....እናቶችም በዕለተ አርብ በሚያደርጉት ንጽሕና፣ ልባዊ ጸሎትና ጽኑ እምነት ምክንያት ያ!...ውኃ የእግዚአብሔር በረከት ይርፍበትና ልጆች ሲታመሙ ወይም ክፉ መንፈስ ሲያስቸግራቸው የሚረጭ፣ የሚጠጣ የፈውስ መሣሪያ (እንደ ጸበል) ይሆናል።     💎 ማጠቃለያ ፦ «የአርብ ውሃ» እናቶች ከቤተክርስቲያን ሥርዓት ተካፍለው ጸበል ማግኘት በማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ እነሰኳ ሳይቀር፣ በቤታቸው ውስጥ ሆነው የክርስቶስን ስቅለትና የመስቀል ላይ በረከት በእምነት የሚሳተፉበት፣ ቤታቸውን ከክፉ ነገር የሚጠብቁበት ጥልቅና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያለው ውብ ክርስቲያናዊ ባህል ነው። ✍️ ዲ/ን ኪዳነ ወልድ

About