@01pa16:

001
001
Open In TikTok:
Region: VN
Sunday 03 May 2026 08:44:47 GMT
215
35
1
1

Music

Download

Comments

mai.duyn83c
💞Khánh 💟Duyên 💞💞💫 :
đi đâu vậy.
2026-05-18 13:23:06
0
To see more videos from user @01pa16, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

በዚህ ቪዲዮዬ የ16ኛው ክፍለ ዘመን በአውሮጳ የተነሳው ሪፎርሜሽን ከጥንቷ ቤተክርስቲያን ያፈነገጠ እንቅስቃሴ ሳይሆን የሃዋሪያቱን አስተምህሮ በጥንቷ ቤተክርስቲያን ውስጥ የነበረውን ዶክትሪን ያስቀጠለ እንቅስቃሴ እንደሆነ ለማሳየት በጥቂቱ ጥረት አደርጋለሁ።  ብዙ ጊዜ የ16ኛው ክፍለ ዘመን ሪፎርሜሽን ከሚተችባቸው የሃሰት ትርክቶች መሃል አንዱ ከሃዋሪያትና ከጥንቷ ቤተክርስቲያን እጅጉን የራቀ ነው በሚል ነው። ይህን ሰንካላ ትርክት በትክክል  ለመረዳት ሁለት ነገር ማወቅ ወሳኝ ይሆናል።  የመጀመሪያው የጥንቷ ቤተክርስቲያን የቆመችበት መሰረታዊ የሆኑ ዶክትሪኖችን ማወቅ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ሪፎርሜሽኑ የቆመባቸው መሰረታዊ የሆኑ አስተምህሮችን በማስተያየት  ከጥንቷ ክርስትና መራቁና አለመራቁን መመርመር ይቻላል።  በነዚህ ሁለቱ ላይ የተንሸዋረረ  መረዳት የሌለው ግለሰብ በትክክል ሪፎርሜሽኑ የሃዋሪያትና የጥንቷን ቤተክርስቲያን አስተምህሮ በሙላት መያዙን በቀላሉ ይረዳል። ይህን አሳቤን በበለጠ ትረዱ ዘንድ በጥቂቱ ላብራራ.  የጥንቷ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ በዋነኝነት የተመሰረተባቸው  ንጣፎች 1 በሃዋሪያት ትውፊት (rule of faith/apostolic tradditions)፣  2 በአለማቀፍ  ጉባኤያት (ecumenical council)፣ 3 የሃይማኖት ድንጋጌዎች (creeds) እና 4 ከኑፋቄዎች (heresies) መለየት ናቸው። እንግዲህ እነዚህ የጥንቷ ቤተክርስቲያን መሰረት የሆኑ የአስተምህሮ ምንጮች ላይ ተመስርተን የ16ኛውን ክፍለ ዘመን የፕሮቴስታንት ተሃድሶን እንቅስቃሴ ለመበየን ሙከራ እናድርግ።  1 ሃዋሪያዊ ትውፊትን በተመለከተ….  በሃዋሪያት በቃልና በጽሁፍ የተሰበከ፣ ለሌሎችም   በእውነት እንዲያስተምሩ አደራ የተሰጡ ትምህርቶች በጥንቷ ቤተክርስቲያን ውስጥ በስፋት እናገኛቸዋለን። አባቶችም ይህን ትውፊት  ከሃዋሪያት መቀበላቸውንና ሌሎችን አስተምህሮ በዚህ መለኪያ እየመዘኑ እንደሚቀበሉ ማረጋገጫ ነው። ይህን አሳቤን እንድትረዱና በቃል ሲተላለፍ የነበረው ሃዋሪያዊው ትውፊት ምን አይነት  ትምህርቶችን እንደያዘ ታውቁ ዘንድ በቅዱስ ኢራኒየስ የተነገረውን ሃዋሪያዊውን ትውፊት ላሳያችሁ።  “For, as to the Church, dispersed as she is through the whole world unto the ends of the earth, yet having received from the Apostles and their disciples the Faith in One God the Father Almighty, Who made the Heaven and the earth and the seas and all that is therein; and in one Christ Jesus, the Son of God, Who was made flesh for our salvation; and in the Holy Ghost, Who by the Prophets declared the Œconomies, and the Advents, and the Birth of a Virgin, and the Passion, and the Rising from the dead, and the bodily Ascension into Heaven of the Beloved, Christ Jesus our Lord, and His Coming from the Heavens in the glory of the Father, to sum up all things and to raise up all flesh of all human nature; that to Christ Jesus, our Lord and God, and Saviour and King, according to the good pleasure of the Invisible Father, every knee may bow, of things in Heaven and in Earth and under the Earth, and that every tongue may confess to Him, and He may administer just judgment to them all; that is, may both send into the everlasting fire the spiritual things of wickedness, as well angels that have transgressed and passed into revolt, as the ungodly and unjust and lawless and blasphemous among men; and also to the righteous and holy, and to such as have kept His commandments and persevered in His love, whether from the first or after penitency, may freely give life, grant incorruption, and compass for them eternal glory:”Against heresy , bk. 1. Chap. X. § 1.  እንዳያችሁ ከዚህ ሃዋሪያዊው ትውፊት ሪፎርሜሽኑ በአንዲትም ነጥብ አይለይም። ይልቁን የሚያጸናቸውና  በትውፊቱ ላይ የተደላደለ አስተምህሮ እንደሚከተል በቀላሉ ትረዳላችሁ።  2 ኢኩሚኒካል ካውንስሎችን በተመለከተ….. ሌለኛው በጥንቷ ቤተክርስቲያን ውስጥ የዶግማ ትምህርቶች  የሚቀዱባቸው ከ ኢኩሚኒካል ጉባኤያት እንደሆኑ በትክክል ይታመናል። ሪፎርሜሽኑ ሙሉ በሙሉ በጥንቷ ቤተክርስቲያን የሚታመኑ አለማቀፍ ጉባኤያትን ማለትም የኒቂያ ጉባኤ፣ የቁስጠንጥኒያ ጉባኤ፣ የኤፌሶን ጉባኤና የኬልቄዶን ጉባኤን ያለምንም የአስተምህሮ ልዩነት ይቀበላል። የተሃድሶ ፍሬ የሆኑ የፕሮቴስታንት ቤተ እምነቶችም መሰረታዊ የሆኑ ኮንፌሽኖቻቸውን በነዚህ ጉባኤያት ላይ የመሰረቱ ናቸው። ከነዚህም  ዶግማ በሆኑ አስተምህሮ የሚቃረን አንድም ትምህርት ሪፎርሜሽኑ አልተቀበለም። 3 የጥንቷን ቤተክርስቲያን የእምነት ድንጋጌዎችን በተመለከተ……  ሪፎርሜሽኑ በጥንቷ ቤተክርስቲያን ውስጥ የተደነገጉ  መሰረታዊ የሆኑ የሃይማኖት ድንጋጌዎችን በሙላት ይቀበላል። እነዚህ የሃይማኖት ድንጋጌዎች የጥንቷ ቤተክርስቲያን ዶግማ የሆኑ አስተምህሮዎችን የያዙ፣ የማይሻሩ፣ ከሃዋሪያት የተቀበሉ፣ በቅዱሳት መጸሃፍት የተመሰከረላቸው ጽኑ የዶግማ ትምህርቶችን  የያዙ ናቸው። እነዚህ የእምነት ድንጋጌዎች የኒቂያና የቁስጠንጥኒያ እምነት ድንጋጌ፣ የሃዋሪያት እምነት ድንጋጌና የአትናቴዎስ እምነት ድንጋጌ ተብሎ የሚጠሩ ናቸው። የታሪካዊው የፕሮቴስታንት ቤተ እምነቶች ሙሉ በሙሉ በነዚህ የእምነት መግለጫዎች ላይ የተመሰረቱ ናቸው።  4 የኑፋቄ ትምህርቶችን በተመለከተ ……. በጥንቷ ቤተክርስቲያን ውስጥ እንደ ኑፋቄ የተቆጠሩ  የስህተት ትምህርቶችን ሪፎርሜሽኑ ሙሉ በሙሉ ከጥንቷ ቤተክርስቲያን ጋር በመሆን የሚያወግዘው እንጂ ተቀብሎ የሚያስተምረው አንድም ኑፋቄ የለውም።  ወዳጆቻችን የሚያቀርቡት ክስ እውነት ቢሆን ኖሮ ፕሮቴስታንቲዝም በጥንቷ ቤተ ክርስቲያን ኑፋቄ ተብሎ በተወገዙ የስህተት ትምህርቶች ውስጥ  መውደቅ በቻለ ነበር።  በተቃራኒው ግን የ16ኛው ክፍለ ዘመን የሪፎርሜሽን እንቅስቃሴ የጥንቷን ቤተክርስቲያን አስተምህሮ የሚያጸናና ከኑፋቄ ትምህርት እጅጉን የራቀ መሆኑን በቀላሉ መረዳት ይቻላል። ስለዚህ የ16ኛው ክፍለ ዘመን ሪፎርሜሽን የወለዳቸው የፕሮቴስታንት ቤተ እምነቶች የሃዋሪያት ትምህርትን በሙላት የያዙና የመጀመሪያይቷ ቤተክርስቲያን አስተምህሮዎችን ያለ ምንም

About