@userashu162: ልዑል አለማየሁ ሚያዚያ 5 ቀን 1853 ዓ.ም በደብረ ታቦር ከተማ ነበር ውልደቱ፡፡ በልዑሉ ውልደት የተደሰቱት አፄ ቴዎድሮስም በእለቱ መድፍ ያስተኮሱ ሲሆን 500 ያህል እስረኞችንም ፈትተዋል፡፡ ከልዑሉ ጋር ሲጫወቱ መዋል አፄውን እጅግ የሚያስደስት ነገር ነበር፡፡ ተናደው እና ተበሳጭተው ከነበር እንኳን አለማየሁን ታቅፈው ሲስሙ ንዴታቸው ይበርድ ነበር ይባላል፡፡ በመቅደላው ጦርነት 1860 የቴዎድሮስ ራሱን ማጥፋት ተከትሎ ልዑል አለማየሁ እንግሊዞች እጅ ከገባ በኋላ ከእድሜው ለጋነት የተነሳ የሚጠብቀው እና የሚንከባከበው ሰው ሊኖር ግድ ነበር፡፡ ይህንን የተረዳው ጀነራል ናፔር ካፕቴን ስፒዲ የተባለን ሰው የአለማየሁ ጠባቂ እንዲሆን መደበው፡ ፡ ምክንያቱ ደግሞ ካፕቴኑ የአማርኛ ቋንቋን አቀላጥፎ መናገሩ ነበር፡፡ በተጨማሪም አለቃ ዝርዓት እና አቶ ገብረመድህን የተባሉ ሁለት ኢትዮጵዊያን ሞግዚቶች እና አጫዋቾች¬ ተመረጡለት፡፡ አለማየሁ ከጠባቂው ስፒዲ ጋር ፌሬዝ በተባለችው መርከብ ተሳፍሮ በ1860 ዓ.ም. ወደ እንግሊዝ አቀና፡፡ በመርከቢቱ ላይ በነበራቸውም ቆይታ ስፒዲ እና አለማሁ እጅግ የጠበቀ ወዳጅነትን መስርተው ነበር፡፡ ስፒዲ በሄደበት ቦታ ሁሉ አለማየሁን ማስከተል ያዘወትር ነበር፡፡ ይህንን የሁለቱን ፍቅር ያየው ጀነራል ናፒየርም ኢትዮጵያውያን ሞግዚቶቹ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ አደረገ ፡፡ ከሶስት ወራት የመርከብ ላይ ጉዞ በኃላ አለማየሁ እንግሊዝ ሀገር ደረሰ፡፡ እዛ አንደደረሰም የወቅቱ የእንግሊዝ ንግስት ከነበረችው ንግስት ቪክቶሪያ ጋር ተገናኘ፡፡ ንግስቲቱም ልዑሉ የፈለገው እና ያሻው ይደረግለት ዘንድ ቀጭን ትዕዛዝ አስተላለፈች፡፡ ልዑሉ በመቅደላ የነበረውን እልቂት በመጠኑም ቢሆን በማየቱ እና የአባቱ እና የእናቱ ተከታታይ ሞትም በልጅ አዕምሮው ሊቀበለው ከሚችለው በላይ ስለነበር እጅግ ታውኮ እንደነበር በተደጋጋሚ ተፅፎ እናገኛለን፡፡ አንድ እንግሊዝ ሀገር ውስጥ በሚገኝ ሙዚየም ውስጥ ባለ የንግስት ቪክቶሪያ የእለት ማስታወሻ ላይም ንግስቲቱ፡ “ምስኪኑ ልጅ አሁንም ፍርሀቱ አለቀቀውም፡፡ ንግስቲቱም የልዑሉን ሁኔታ በቅርበት ትከታተል ነበር፡፡ ስፒዲ ልጁን እንዳይጎዳው በማሰብም በስፒዲ ላይ የልዑሉን ጉዳይ በቅርበት የሚከታተል ተቆጣጣሪ አስቀምጠውበት ነበር ይባላል፡፡ አንድ ግዜ ንግስት ቪክቶሪያ ስለ ልዑሉ በእለት ውሎ መመዝገቢያዋ ላይ ከመዘገበችው መሀል “ልጁ ጨዋ እና ውብ ልጅ ነው፡፡ ኬክ መብላት ደግሞ ይወዳል። የሰጠሁትንም ኬክ ሁሉ ጨርሶ በላ፡፡” የሚል አረፍተ ነገር ተፅፎ እናገኛለን፡፡ ንግስቲቱ በተደጋጋሚ ለዚህ እናት ለሌለው ልጅ እናቱ እኔ ነኝ ስትል ትደመጣለች፡፡ ለልዑሉም የተለየ አክብሮት እና ፍቅር ፤ ልዩ ትኩረትም እንደነበራት ድርሳናት ዘግበውታል፡፡ ምንም እንኳን ከንግስቲቱ ጋር የነበራቸው ወዳጅነት ከግዜ ወደ ግዜ እየበረታ ቢመጣም ከሀገሩ ሲወጣ አብሮት የነበረውን ካፕቴን ስፒዲን ግን ለአፍታም አልዘነጋውም ነበር፡፡ በየትኘውም ስፍራ ሲሄድ ስፒዲ አብሮት እንዲሆን ይፈልጋል፡፡ ግብዣም ሲሄድ ሆነ ከልዑላን ልጆች ጋር እንዲጫወት ሲጋበዝ ስፒዲን ትቶ መሄድ አይሆንለትም፡ ፡ ቤተ-መንግስት ሲገባ እንኳን ስፒዲን አስከትሎ ነው፡፡ ስፒዲ እና አለማየሁ አብረው ይበላሉ አብረውም ደግሞ ይተኛሉ፡፡ አለማየሁን ለብቻው ማሳደግ የከበደው ስፒዲ ልጁን በማሳደግ ትረዳው ዘንድ ሚስት ለማግባት ወሰነ፡፡ ከዛም ወ/ሮ ኮታንን አገኘ እና አገባት፡፡ አለማየሁ እና ወ/ሮ ኮታንም ለመዋደድ ግዜ አልወሰደባቸውም ነበር፡፡ በ1861 ዓ.ም ስፒዲ ህንድ ሀገር በምትገኝ አንዲት ከተማ አዛዥ ሆኖ ስለተሾመ የ8 ዓመቱን አለማየሁን እና ሚስቱን ይዞ ወደዛው አቀና፡፡ በሄዱበት ሀገርም አለማየሁ ትምህርቱን መከታተሉን ቀጥሎ የነበረ ሲሆን ከመደበኛው ትምህርት በዘለለም ፈረስ ግልቢያ እና ሌሎች ስፖርቶችንም ያዘወትር ነበር፡፡ ልዑሉ በዚህ አይነት ከቆየ በኃላ ቻንስለር ሮበርት ሉዊ ልዑሉ የቀለም ትምህርት ላይ ከሚያዘወትር ይልቅ የወታደር ትምህርት ቤት ገብቶ የፈረስ ውትድርናን እንዲማር መደረግ አለበት ሲሉ ያቀረቡት ሀሳብ የልዑሉን ህይወት እስከወዲያኛው የለወጠ ነበር፡፡ ይህም ሀሳብ ተቀባይነትን ስላገኘ አለማየሁን ከስፒዲ ነጥሎ በመንግስት ቁጥጥር ስር ለማድረግ እና የውትድርና ትምህርቱን እንዲከታተል ተወሰነ፡፡ ይህ ውሳኔ ግን ለአለማየሁም ሆነ ለስፒዲ ከባድ ግዜ ነበር፡፡ ስፒዲ እና ሚስቱ አለማየሁን ላለመስጠት ከባድ ትግል አደረጉ፡፡ ነገር ግን ትግላቸው ውጤትን አላስገኘላቸውም፡፡ አለማየሁ ወደ እንግሊዝ ሀገር እንዲመለስ ተወሰነ፡፡ ስፒዲም አለማየሁን ይዞ ወደ እንግሊዝ መጣ፡፡ የአለማየሁ አዲሱ አስተማሪ እና ጠባቂ እንዲሆኑ የተመረጡትም በአስተማሪነታቸው የተመሰከረላቸው እና በደግነታቸው የታወቁት ቄስ ብሌክ ነበሩ፡፡ ንግስት ቪክቶሪያም የአለማየሁን እና የስፒዲን ፍቅር ያውቁ ስለነበር ሁለቱን ቶሎ መነጣጠል አልፈለጉም፡፡ ይልቁኑም አለማየሁ ከቄስ ብሌክ ጋር እስኪላመድ ድረስ ስፒዲ አብሮት ይቆይ ስትል ፈቀደች፡፡ አዲሶቹ የአለማየሁ ጠባቂዎች አለማየሁ ስራ እንዲሰራ ወሰኑ፡፡ በወጣለትም ፈረቃ መሰረት በሳምንት ለ 31 ሰዓት ተኩል ያህል ማንኛውንም አይነት ስራ እንዲሰራ ተወሰነ፡ ፡ የስፒዲ ሚስትም ይህንን በመቃወም ጠባቂው ለነበሩት ቢዶልፍ ደብዳቤ ላከች፡፡ ቢዶልፍም ልዑል አለማየሁ አንዳንድ ግዜ እየሄደ ከስፒዲ ሚስት ጋር ግዜ እንዲያሳልፍ ሲሉ ትዕዛዝ አስተላለፉ፡፡ በትዕዛዙም መሰረት የስፒዲ ሚስት ከአለማየሁ ጋር እንድትውል ተፈቀደላት፡፡ ሚስቱም አብራ ውላ ያየችውን እንዲህ ስትል በደብዳቤ ገልጣለች፡ “ማደጉን ቁመቱ አድጓል፡፡ መልኩ ግን ገርጥቷል፡፡ አካላቱም ከስቷል፡፡ ዝምተኛ እና ጭምትም ሆኗል፡፡ ከወንዶች ልጆች ጋር እንዳይገናኝ እና ከእኩዮቹም ጋር እንዳይገናኝ ተደርጓል፡ ፡ ውጪ እየወጣም እንዳይዘል ታግዷል፡፡ እየደጋገመም ‘አብረውኝ የሚጫወቱ ልጆች አጣሁ፡፡ ” የስፒዲ ሚስት የፃፈችው ይህ ደብዳቤ ከንግስት ቪክቶሪያ ዘንድ ደረሰ፡፡ ንግስቲቱም ትንሹ ልዑል አብሮአቸው ሊጫወት የሚችሉ ጓደኞች እንዲፈለጉለት አዘዘች፡፡ እንደተባለውም ተደረገ፡፡ 1867 ዓ.ም አለማየሁ ወደ ራግቢ ትምህርት ቤት ተዛወረ፡ ፡ በዚህም ከቄስ ብሌክ ቤት ወጥቶ ወደ ሊው ዋርነር ቤት እንዲገባ ተደረገ፡፡ በዚህ ግን ደስተኛ ስላልነበር በቀጣዩ አመት ሚስተር ድራፐር ቤት እንዲኖር ተደረገ፡፡ ቄስ ብሌክም ካዩት የልዑሉ ባህሪ በመነሳት ልዑሉ ወታደርነት ላይ ቢያተኩር የበለጠ ውጤታማ እንደሚሆን ተናገሩ፡፡ በዚህም ንግግር መሰረት የወታደር ትምህርት ቤት እንዲገባ ተደረገ፡፡ በአንድ ወቅት አለማየሁ ወደ ሊድስ በመሄድ በሰር ራምሰን ቤት ተቀምጦ በነበረበት ወቅት በመርዝ ተመረዘ። (በኢንፍሎንዛ ) የሚሉ አሉ መርዙ ህዳር 5 ቀን 1872 ዓ.ም ከጠዋቱ በ3 ሰዓት ከሩብ በተወለደ በ19 ዓመቱ ከዚህ አለም እንዲሰናበት አደረገው፡፡ አስከሬኑም ዊንድሶር ባለው የነገስታት መቀበርያ በክብር አረፈ፡፡ በመቃብሩም ላይ “የሀበሻው ልዑል አለማየሁ” የሚል ፅሁፍ ሰፍሮበት እስካሁን በእንግሊዝ ሀገር ይገኛል፡፡ ምንጭ የአፄ ቴዎድሮስ ታሪክ #foryou #ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 #fypシ #foryourpage #viraltiktok
መኃልዬ መኃልዬ ዘኩማንዳ ጠባ
Region: ET
Friday 12 June 2026 18:32:56 GMT
Music
Download
Comments
Travel with Abrish :
why ,always , after i read about this prince ,feel sad 😰
2026-06-12 18:46:06
5
የኔ ዓለም ሲራክ :
❤️🙏❤️
2026-06-13 06:15:58
1
እመን አማራዊት የየጁዋ✍🏽🦅 :
🥰🥰🥰🥰🥰
2026-06-12 20:21:52
1
bushemelese6 :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-06-12 19:11:48
1
moges046 :
🥰🥰🥰
2026-06-14 09:00:43
1
Yeju🦅(pain) :
🥰🥰
2026-06-12 22:52:56
1
Zema Ti :
🙏🙏🙏
2026-06-14 05:19:57
1
🇦🇹🇦🇹የአፄወቹ🇦🇹🇦🇹💚💛❤️ :
❤️❤️❤️
2026-06-12 18:46:05
1
Habtamu Asres :
💪💪💪💪💪❤️❤️❤️
2026-06-13 18:57:15
1
tige :
🥰🥰🥰🥰🥰
2026-07-10 10:17:07
0
Log Out :
💪💪💪
2026-07-19 07:43:44
1
To see more videos from user @userashu162, please go to the Tikwm
homepage.