@hilasolomon_1:

Hilasolomon
Hilasolomon
Open In TikTok:
Region: IL
Saturday 13 June 2026 21:49:27 GMT
1121
86
1
8

Music

Download

Comments

To see more videos from user @hilasolomon_1, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

አንዳንድ ጊዜ...እኛን ወደ ኋላ የሚጎትተን ድህነት ብቻ አይደለም። ዕድል ማጣትም ብቻም  አይደለም። አስተሳሰባችን ነው። እውነትን...በቀጥታ ከመናገር...ከጀርባ ማውራትን እንመርጣለን። ችግር ሲፈጠር...ተቀምጠን መወያየትን ሳይሆን... ሀሜትን እናስቀድማለን። ሰው ሲሳካለት ...
አንዳንድ ጊዜ...እኛን ወደ ኋላ የሚጎትተን ድህነት ብቻ አይደለም። ዕድል ማጣትም ብቻም አይደለም። አስተሳሰባችን ነው። እውነትን...በቀጥታ ከመናገር...ከጀርባ ማውራትን እንመርጣለን። ችግር ሲፈጠር...ተቀምጠን መወያየትን ሳይሆን... ሀሜትን እናስቀድማለን። ሰው ሲሳካለት ..."እንኳን ደስ አለህ!" ከማለት ይልቅ... "እንዴት አገኘው?" ብለን መጠራጠርን እናስቀድማለን። ሰው ሲወድቅ ...ለማንሳት ከመሞከር...የወደቀበትን ለማሳየት እንጣደፋለን። የሌላ ሰው ስኬት...ራሳችን መነሳሳት መሆን ሲገባው አንዳንድ ጊዜ...የልባችን ሸክም ይሆናል። ምቀኝነት... በመጀመሪያ የሚያቃጥለው የምንቀናበትን ሰው አይደለም። የራሳችንን ልብ ነው። ሀሜት...ሌላውን ከመጉዳቷ በፊት የራሳችንን ባህርይ ታጎድፋለች። ውሸት...አንድ ጊዜ ሰውን ሊያታልል ይችላል። ግን...እውነት በመጨረሻ ሁልጊዜ ትቆማለች። እያንዳንዳችን..."እነሱ ይለወጡ" እንላለን። ነገር ግን...ማንም..."እኔ ልለወጥ" ማለት አይፈልግም። የማህበረሰብ ለውጥ...በመንግሥት ብቻ አይጀምርም። በቤታችን...በቃላችን...በአስተሳሰባችን... በየቀኑ በምንመርጠው ባህርይ ይጀምራል። ሰው ሲሳካለት...እንደራሳችን ደስ ይበለን። እንደው ደስ ባይለን እንኳን አይክፋን። ሰው ሲሳሳት...ከመሳቅ ይልቅ እናርመው። ልዩነት ሲኖር...ከሀሜት ይልቅ ውይይትን እንምረጥ። ከጀርባ ከመናገር...ፊት ለፊት በአክብሮት መናገርን እንልመድ። ምክንያቱም...የተሻለ ማህበረሰብ በተሻሉ ሰዎች ይገነባል። የተሻሉ ሰዎች ደግሞ ራሳቸውን ለመለወጥ በሚወስኑ ሰዎች ይጀምራሉ። ስለዚህ... ከሌሎች በፊት...ራሳችንን እንጠይቅ። ከሌሎች በፊት...ራሳችንን እናርም። ምክንያቱም...ሕዝብ የሚለወጠው አንድ ሰው በአንድ ሰው ሲለወጥ ነው። ይህ የእኔ እይታ ነው ✍️ ሰናይ ቀን ቀጣይ ሌሎች እይታዎች እንዲደርስዎት የእኔ እይታን ፔጅ Follow, Like, Share, Repost እና Copy Link በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ! #foryou #fyp #viral #fypシ #viralvideo

About