@maki.papa3: 🛀🧼🚿 ሻወር ስንወስድ የምንሰራቸው 10 የተለመዱ ስህተቶች! | Common Shower Mistakes That May Harm Your Skin & Health! 🚿💦 ገላን መታጠብ ወይም ሻወር መውሰድ የዕለት ተዕለት ተግባራችን አካል ነው። ነገር ግን አንዳንዴ በልማድ የምናደርጋቸው የተሳሳቱ ነገሮች፦ ለቆዳችን፣ ለፀጉራችን፣ ለሰውነት ንጽህናችን፣ እና ለአጠቃላይ ጤንነታችን ጎጂ ሊሆኑ ይችላሉ። የቆዳችንን ውበት እና ጤንነታችንን ለመጠበቅ እነዚህን 10 ስህተቶች ከማድረግ ይቆጠቡ፦ ✅🚿 ሻወር ስንወስድ የምንሰራቸው 10 ስህተቶች! | 10 Mistakes We Make When Taking a Shower! 1️⃣. 🚿 በጣም በሞቀ ውሃ መታጠብ! | Taking Very Hot Showers! በጣም በሞቀ (በሙቅ ውሃ) መታጠብ ደስ የሚል ስሜት ሊሰጥ/ሊፈጥር ቢችልም፤ የቆዳችንን ተፈጥሯዊ ቅባት በማስወገድ ለቆዳ መድረቅ፣ ለቆዳ ማሳከክ፣ እና ለቆዳ መቆጣት ይዳርጋል። ስለዚህ ከሙቅ ውሃ ይልቅ ለብ ያለ ውሃ መጠቀም ይመከራል። 2️⃣⏳ ለረጅም ሰዓት ሻወር ውስጥ መቆየት! | Showering for Too Long! ⏳ ገላን በመታጠብ ረጅም ሰዓት መቆየት ወይም ለረጅም ጊዜ ሻወር መውሰድ፤ የቆዳን እርጥበት የሚጠብቁ ተፈጥሯዊ ቅባቶችን ወይም ዘይቶችን ጠራርጎ ያስወግዳል። የመታጠቢያ ጊዜዎን ወይም ሻወር የሚወስዱበትን ጊዜ አጭር በማድረግ የቆዳዎን ልስላሴና እርጥበት መጠበቅ ይችላሉ። 3️⃣🧼 ከመጠን በላይ ሳሙና ወይም ኃይለኛ ኬሚካሎች መጠቀም! | Using Too Much Soap or Harsh Products! 🧼 ጠንካራ ሳሙናዎች እና ኬሚካል ያላቸው ማጽጃዎች የቆዳችንን ተፈጥሯዊ መከላከያ ንብርብር ሊጎዱ ይችላሉ። በተለይ ቶሎ የሚቆጣ (sensitive) ቆዳ ካለዎት፤ ለስላሳ ምርቶችን እና ተፈጥሯዊ የሆኑ ሳሙናዎችን ይምረጡ። 4️⃣🧽 ቆዳን በኃይል መፈግፈግ! | Scrubbing Too Hard! 🧽 ቆዳን በሃይል መፈግፈግ (መፈተግ) የቆዳ መቆጣት እና ጥቃቅን የመላጥ አደጋዎችን ወይም ቁስለቶችን ሊያስከትል ይችላል። ሰውነትዎን በሚታጠቡበት ወቅት በጣም ሳያጠብቁ በለሰለሰ መንገድ (በስሱ) ማጽዳት መታጠብ ያስፈልጋል። 5️⃣🪒 ጸጉርን በተሳሳተ መንገድ መላጨት! | Shaving the Wrong Way! 🪒 ቆዳ ሳይረጥብ (በደረቁ) መላጨት ወይም የደነዘዘ ምላጭ/ማሽን መጠቀም፤ የቆዳ መቀደድ (መቁሰል/መቆረጥ)፣ የቆዳ መቆጣት፣ እንዲሁም ፀጉር ወደ ውስጥ እንዲያድግ ያደርጋል። ሁልጊዜም ለመላጨት የሚያገለግል ክሬሞችን (Shaving Cream) ወይም ጄሎችን፣ እንዲሁም ንጹህና አዲስ ምላጭ ይጠቀሙ። 6️⃣🧴 ከሻወር በኋላ ሎሽን/ቅባት አለመቀባት! | Forgetting Moisturizer After Showering! 🧴 ከሻወር እንደወጡ ቆዳዎ በመጠኑ እርጥበት እንዳለው (ሰውነትዎ ሳይደርቅ) ሎሽን ወይም ማለስለሻ ቅባት መቀባት፤ የቆዳን እርጥበት ጠብቆ ለማቆየት እና የቆዳ መድረቅን ለመከላከል ይረዳል። 7️⃣🧼 የሻወር ዕቃዎችን/ቁሳቁሶችን አለማፅዳት! | Not Cleaning Your Shower Items! 🧼 ገላ መፈግፈጊያ ስፖንጅ፣ የሻወር መታሻ፣ እና ሌሎች መታጠቢያ ዕቃዎች በአግባቡ ካልጸዱ እና ካልደረቁ የባክቴሪያዎች መራቢያ ሊሆኑ ይችላሉ። ስለዚህ በየጊዜው ማጽዳትና ማድረቅዎን አይዘንጉ። 8️⃣🚿 ፎጣን በየጊዜው በአግባቡ አለማጠብ! | Not Washing Your Towel Properly! 🚿 እርጥብ ፎጣ ለጀርሞች እና ለፈንገስ መራቢያ ምቹ ቦታ ነው። ፎጣዎን አዘውትረው ይጠቡ፤ ከተጠቀሙ በኋላም ሙሉ በሙሉ በሚገባ እንዲደርቁ ያድርጉ። 9️⃣🦶 እግርን መዘንጋት ወይም መርሳት! | Ignoring Your Feet! አብዛኛው ሰው ሻወር በሚወስድበት ጊዜ እግሩን በደንብ አይታጠብም። በተለይ በጣቶች መካከል ያለውን ቦታ (የጣትና የጣትን መሃል) በሚገባ ማጠብና ማድረቅ ከፈንገስ (Fungal) ኢንፌክሽኖች/በሽታዎች ይጠብቃል። 🔟🧴 የግል የሻወር ዕቃዎችን ከሌሎች ጋር በጋራ መጠቀም! | Sharing Personal Shower Items! 🧴 እንደ ምላጭ፣ ፎጣ፣ እና ሌሎች መሰል የግል ንጽህና መጠበቂያ ዕቃዎችን በጋራ መጠቀም፤ የቆዳ በሽታዎችን እና የተለያዩ ጀርሞችን በቀላሉ ሊያስተላልፍ ይችላል። 🌧️☔️ ጤናማ የሻወር ልማድ ማለት፦ ረጅም ሰዓት መታጠብ ወይም (ሻወር ውስጥ ብዙ ሰዓት ማሳለፍ) ሳይሆን፤ የተሻሉና ጤናማ ልማዶችን መከተል ማለት ነው። 💧

The bastard
The bastard
Open In TikTok:
Region: ET
Monday 29 June 2026 16:05:30 GMT
258782
5319
103
599

Music

Download

Comments

ela74344
ela :
vjchfghhg😭😂😳😏😁🥰
2026-07-20 09:08:07
0
aktro.gym
Aktro Martins :
Thanks 🙏🙏🙏
2026-07-21 06:16:20
0
eshet.man0
Eshet Man :
አልገባኝም
2026-07-21 12:02:20
1
natnael.zemene03
Natnael zemene 03 :
አልገባኝም
2026-07-01 09:00:49
7
favutesfa1
fevu beuty salon1 :
yetejajale hasab
2026-07-01 10:48:17
3
brhaneabi
brhane🇧🇴🇧🇴💋 myborena🇳🇮 :
2026-06-30 18:01:55
3
ankitrawal243
jo tattoo :
11ኛ አድነገር ይቀራል
2026-07-02 10:15:53
3
user6336903160927
ኤቴርወ በጔታ የሸገር ተፈናቃይ :
እናመሰግናለን
2026-06-30 12:25:05
5
endalk376
endalk :
በጣም ጠቃሚ ማርያምን
2026-07-03 00:45:41
1
ababayyo.mitikkuu
@5mitiku :
እናመስህናለን🙏🙏🙏🙏
2026-07-01 12:45:59
3
sulymen0913810553
ሱለይማን ሰይድ :
አልመጠልኝም
2026-07-01 17:28:17
3
be43063
bez top sho :
ደስ የሚል ግንዛቤ 🥰🥰
2026-07-01 14:37:26
3
brukzewudu828
egle🦅❤️❤️ :
1ኛ ውን ስህተት ደጋግሜ ምሰራው እኔ😁😁
2026-07-02 03:25:49
2
natanim.g.meskel
Natanim G.meskel :
እናመሰግን አለን
2026-07-06 09:02:51
1
habtamuyirga921
habte@123 :
Wawww Tiru Tmihrt new
2026-07-01 15:25:09
2
china65310
china ነኝ ጎንደሬው 💚💛❤️🇪🇹🇪🇹 :
እናመሰግናለን
2026-07-01 12:41:38
2
bilen0992
Bilen yemariyam :
2 እኔ 😳
2026-07-05 09:00:18
1
brhaneabi
brhane🇧🇴🇧🇴💋 myborena🇳🇮 :
tekiw🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-06-30 18:02:18
1
maki12917
M.e.k.d.i @12 :
ሁሌም የምዘፍነው እኔ😁🥰
2026-07-02 03:15:48
2
tsige7607
Tsige :
እናመሰግናለን
2026-07-01 12:13:09
1
ahadubirhane
Birhane :
waw
2026-07-01 13:01:09
1
user61833702983324
mekdi :
የታሉ
2026-07-01 11:57:44
2
ggww2121
gw man :
tank you 🙏🙏🙏
2026-07-01 11:47:10
1
mame10045
محمد الحبشي ❤ :
10Q🥰🥰🥰
2026-07-01 07:13:57
3
tirengoye1
tirengoye :
አልገባኝም
2026-07-02 11:38:32
1
To see more videos from user @maki.papa3, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About