@muba__fx: "ለምንድነው ድንገት የተውከኝ አለቺኝ ?" "እኔ'ንጃ ምን አልባት ፈርቼሽ ይሆናል"። በአይኗ እየተቅለሰለሰች "ምኔ አስፈራህ ትባ'ላለች አሉህ ወይ " ጥቁረቷ የዐይኗን ውበት ጨምሮታል ጥቁረቷ ጥርሷን ጥርሰ በረዶ ናት እንድትባል ያደረጋት ይመስለኛል። ስታምር ! ትክ ብዬ እያየኋት "የመወደድ ርኃብ ያለብሽ ይመስላል "አልኳት ምን ማለት ነው ?? "የሚወደኝ አጥቼ ማለት ነው? " ሳቀች አሳሳቋ ፌዝ አዝሏል አይምሰልሽ የአንዳንድ ርሃብ ምንጭ እኮ የአቅርቦት እጥረት አይደለም የአስተዳደግ ጠባሳም ሊሆን ይችላል። ቀጠሮ ኖርበት የክት ልብሱን አጥቦ ፀሃይን እንደሚጠብቅ ሰው ነው ቀልብሽ ቆሌሽ ሁሉ ነገርሽ መወደድሽን የሚጠብቀው .... እመኚኝ ቲጂ ማስከተል ለምደሻል ... ፍላጎት አምጠሽ ፣አስወልደሽ ፣አሳድገሽ እንዳላወቀ ድንግጥ ብለሽ እንዴት እንደዚህ ሊሰማ ቻለ !? ብለሽ መካድ ለምደሻል ! . ለመወደድ ምቹ ሆኖ ጠዋት ማታ ከለፉ በኃላ በዚህ መንገድ አላሰብኩም ብለው ከሚያለግጡት ውስጥ ነሽ ከልብ ያሆነ ፈገግታ ፊቷ ላይ ብርት ብሎ ጠፋ ....."ያንተ ጠላት አንተ ነህ መታገስ ሲያቅትህ ለመሸሽ የሰጠህኸው ሰበብ ነው ግርማ እመነኝ የማጣት ፍርሃት አለብህ ...." አይ ቲጂ እኔ የማቃጥለው ትርፍ ግዜ የለኝም !! የመታኝን አይነት እንቅፋት እንዳየሁት ነው የማውቀው ከነ ህመሙ ነው የማስታውሰው እኔ የሰው trauma ማከም አቅም ላይ አይደለሁም ...! አሁን ባላሁበት ሁኔታ አልችልሽም ያሸሸኝ የአቅም ጉዳይ ነው ... መንገድሽን ዞር ብለሽ እይው ሲርቁሽ የምትከትየው እና ሲቀርቡሽ የምትርቂው ርቀት ተመሳሳይ ይመስለኛል ፈራሁሽ !! እንዳንቺ አይነት ሰዎች እንደተወደዱ ካረጋገጡ በኋላ ቀስስ ብለው ከሪትሙ ይወጣሉ ለመወደድ ያደረጉት የከፈቱትን ሁሉ ዝግትግት ያደርጋሉ ... Look ... መጀመርያ ሰሞን እምቶኝልኝ ነገር ሁሉ እንደእጮኛሽ ነው ፣ የመጀመርያ ሰሞን የምታወሪበት ድምፅት እንኳን የለም ። እንክብካቤሽ፣ መንገድ ስንሄድ ሽጉጥ የምትይብኝ ፣መውድድሽ በየምክንያቱ ማክበርሽን በየስበቡ የምታሳይኝ ነገር ሁሉ ራሱን አጥፍቷል። የመንገደኛን ኮቴ መከተል አልችለም ትኩረቴን የሚሻ ህልም አለኝ የኔን ግዜ የሚፈልግ ሌላ ትግል አለኝ። "በኔ አታሳብ ግርምሽ ቶሎ መወደድ ለምደህ ነው!! ሳጠይቅ ማግኘት አበላሽቶህ ነው!! ሳትበረታ ላጣኸው ሁሉ ያንተ ጥፋት እንዳልሆነ ለጭንቅላትህ መንገር ለምደህ ነው ።ድክመቱን ሁሉ የሰው ችግር አድርጎ እንደሚተነትን የሚያሳዝነኝ የለም ።" ቲጂዬ እውነትሽን ነው አቅም ስለሌለኝ ነው የሸሸሁት። ከማልችለው ጋ ምን አታገለኝ ብዬ ነው !! አንቺ ደሞ ሁኔታሽ ሁሉ እንደወፍ ነው ሲከተሉሽ ትበርያለሽ ስረጋጋ ስቆም መጥተሽ አናቴ ላይ ትወጫለሽ ደስታ ሊያስደንሰኝ ሲጀምር ትበርያለሽ ... እንደቅድሙ አልሳቀችም .... "ዳንስ መቼ ትችል እና ...ይልቅ ግርምሽ ሪስክ የማይወስድ ሰው አልወድም ፣ የተበላሸ ነገር ለመስራት የማያቅድ ወንድ ፤ የተሰራ ነገር የሚያሳድድ ሰው ያሳዝነኛል በተለይ ወንድ ...." ካንቺ ባላቅም ....! ጀግና የሚያተርፈውን ሳያሰላ አይታገልም ። ጀግና ሁኔታን እና ዋጋን አስልቶም ይሸሻል እስከማውቀው .... አለም ላይ የመወደድ ርሃብ ካለበት ሰው ጋ እንደተጣበሰ ፣ እንደተጋባ የሚያሳዝነኝ የለም ... ጠዋት ማታ ሥራ አለበት፥ ማባልል አለበት፥ ውድድር አለበት ኑሮ ሁሉ ሪሲሊንግ በይው...ዋንጫ ሜዳልያ የማይበላበት ሪሲሊንግ "ማንም እንዲ ብሎኝ የትኛውም ወንድ አንተ ባልከው መንገድ ተረድቶኝ አያውቅም !" ይሆናል .....እኔ ግን አንተ ብቻ ነህ ያመለጥከኝ እንዳልሺኝ ነው የምቆጥረው !! © Adhanom Mitiku #ግጥም_በግጥም🥰 #ግጥም #ግጥምለምትወዱ #ገጣሚ_ኤልያስ_ሽታሁን

የግጥም አብዮት 🫀✍️
የግጥም አብዮት 🫀✍️
Open In TikTok:
Region: ET
Saturday 18 July 2026 18:54:25 GMT
6083
334
4
18

Music

Download

Comments

fish7431
fish :
wawww🥰👍
2026-07-19 18:09:41
0
henniqua1
Henni :
ጀግና ማያተርፈውን ሳያሰላ አይታገልም👌
2026-07-19 18:45:19
0
ygere741
Yehowala :
የመወደድ ረሀብ አለብሽ... የማጣት ፍርሀት አለብህ....👌
2026-07-19 15:25:12
0
amen5307
Amen :
😞😞😞😞😞
2026-07-19 18:37:45
0
To see more videos from user @muba__fx, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About