@trangshopping99: #youthology #daugoiyouthology #daugoichonggau #daugoikiemdau #sachgaubet

𓍼 𝕿𝖗𝖆𝖓𝖌݁ 𓇼ꫂ ၴႅၴ
𓍼 𝕿𝖗𝖆𝖓𝖌݁ 𓇼ꫂ ၴႅၴ
Open In TikTok:
Region: VN
Monday 10 August 2026 14:20:23 GMT
314
2
1
0

Music

Download

Comments

trangshopping99
𓍼 𝕿𝖗𝖆𝖓𝖌݁ 𓇼ꫂ ၴႅၴ :
💯💯💯💯💯💯💯💯💯
2026-08-10 14:20:46
0
To see more videos from user @trangshopping99, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

ባል ስጠኝ ብዬማ እግዚአብሔርን አለምንም  አንብቡት በእመቤቴ ዛሬ ያገኘኋት ወጣት እህቴ ስለ ግል ሕይወቷ በግልጽነትና በፍጹም በራስ መተማመን ስታወራኝ ቆየች። እናም እንዲህ በማለት ጠየቀችኝ
ባል ስጠኝ ብዬማ እግዚአብሔርን አለምንም አንብቡት በእመቤቴ ዛሬ ያገኘኋት ወጣት እህቴ ስለ ግል ሕይወቷ በግልጽነትና በፍጹም በራስ መተማመን ስታወራኝ ቆየች። እናም እንዲህ በማለት ጠየቀችኝ "እውነቴን ነው የምልህ እግዚአብሔርን የሚፈራ ለትዳሩ ክብር ያለው ባል ባገኝ ደስ ይለኛል። በተለይ በቁርባን ባገባ በጣም ደስ ይለኛል። ነገር ግን ይኼን ማግኘት በጣም ከባድ ነው። የሚታመን ወንድ የለም አለች። እኔም እጅግ መልካም ነገር ተመኝተሻል። ምኞትሽ እንዲሳካ ለምን ታዲያ እግዚአብሔር የምትመኚውን መልካም ሰው እንዲሰጥሽ በጸሎት አትጠይቂውም አልኳት። እርሷም ኸረ እንደ ደግሞ እግዚአብሔርን ወንድ ስጠኝ ባል ስጠኝ ብዬ ልለምነው እንዴ? ኸረ በፍጹም! እግዚአብሔርን እማ ባል ስጠኝ ብዬ አለምንም" ስትል አጽንኦት በመስጠት አቋም" በሚመስል ድምጸት ነገረችኝ። ይህ አይነት አረዳድ የእርሷ ብቻ ሳይሆን የብዙ እህቶችና ወንድሞች አረዳድ ነው። ለዛ ነው በአንድ ወቅት አንዲት ልጂ ባል ትፈልግና ሃይማኖቷ በሚፈቅደው ሕግና ስርዓት መሠረት ዘወትር ወደ እግዚአብሔር ትጸልያለች። ዳሩ ግን አንድም ቀን እግዚአብሔርን በቀጥታ ጥሩ ባል ጥሩ ትዳር እንዲሰጣት ለምናው አታውቅም። ለምን ቢባል ታፍራለች። "እግዚአብሔር እንደት ስለ ባል ይጠየቃል? የሚል ደካማ አመለካከት አላት። እግዚአብሔርንም ጥሩ ባል ስጠኝ ብላ መለመን ያሳፍራታል። እንዳትተወው ደግሞ ባል ያስፈልጋታል ታዲያ አንድ ቀን ሲጨንቃት እንዲህ ብላ ጸለየች፤ ፈጣሪዬ እባክህን ለእናቴ ጥሩ አማች ስጣት" የምባረክበት፣ አንተም የምትከብርበት መልካምና አንተን የሚፈራ ሃይማኖቱን የሚወድ ባል ስጠኝ ላለማለት "አማች ስጣት ያለችው። እህቴንም የገጠማት ይኸው ነበር። ብዙ ጊዜ ገንዘብ፣ ሥራ ወዘተ የመሰሉ ነገሮችን ስጠኝ ብለን ለመለመን አናፍርም። ወንዱ ሚስት ሴቷ ደግሞ ባል ስጠኝ ብለው መለመን እግዚአብሔርን ያፍራሉ። ይኼ ፍጹም ስሕተት ነው። ጋብቻ ክቡር ነው መኝታውም ንጹሕና ቅዱስ ነው። እግዚአብሔርን የምትፈራ ሚስት በጸሎት ካልሆነ ከየት ልትገኝ ትችላለች? ባልም እንደዛው። ጋብቻ ታላቅ ምስጢር ነው። ጋብቻ ለቤተ ክህነትም ለቤተ መንግሥትም የሚሆኑ ልጆች የሚፈሩበት ነው። ጋብቻ ትልቅ አቋም ነው። ሚስት የእስከ ሕይወት ፍጻሜ የሀዘንም የደስታም ተካፋይ የሕይወት አጋር ናት። ባልም እንዲሁ። ታዲያ ይኼን ትልቅ ጉዳይ እግዚአብሔር አባታችንን ካልጠየቅን ማንን ልጠይቅ ነው? መልሱ ማንንም ነው። ባል የሚሆን ወንድ የለም ከማለት ሚስት ሆኖ ተገኝቶ ባል እንዲሰጥሽ እግዚአብሔርን መለመን። አንተም ወንድሜ እንደዛው። ከእህቴ ጋር ብዙ ተወያይተንበት በመጨረሻም "ኸረ እንዲያም እንዲህ ከሆነማ በጸሎት ብቻ ሳይሆን በሱባኤም ጭምር ነው የምጠይቀው ብላኝ ተለያየን። በእርግጥ እግዚአብሔርን ስንለምን "የምትለምኑትን አታውቁምን" ተብለው እንደተወቀሱ ሰዎች እንዳልሆን መጠንቀቅ አለብን። ለብዙዎች ግን የሚያሳፍረው ሳያሳፍራቸው ፤ የማያሳፍረው ያሳፍራቸዋል። ወሰብሐት ለእግዚአብሔር ወለ ወላዲቱ ድንግል ወለ መስቀሉ ክቡር አሜን

About