@famkm21:

FAMKM
FAMKM
Open In TikTok:
Region: SA
Monday 17 August 2026 04:55:01 GMT
33397
40
1
9

Music

Download

Comments

jahangirvai651
👷‍♂️🇧🇩Jahangir🇸🇦👷‍♂️ :
🥰🥰
2026-08-19 20:08:19
0
To see more videos from user @famkm21, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

የኩኩ 1998
የኩኩ 1998 "ትዝታ" አልበም one My favorite Album ❤ ~ ዘፈኖቹ ወደ ኋላም ይስባሉ የዘፈኑ ግጥሞች የሚፈጥሩት ምስልና የሚነግሩን ታሪክ እንደ ፊልም በአዕምሯችን እንድንስል ያደረገናል! ~ታዲያ ከአልበሙ ውስጥ "ወሎ" የሚለው ዘፈኗም ምስል ከሳች ነው....ከልጅነት አብሮ አደጓ ጋር ያሳለፉትን ጊዜና ያደጉበትን ሰፈር ከዛ እየተፋቀሩና እየተዋደዱ እንዴት እንደተለያዩ...ከእሱ ተለይታ ለሌላ እንዴት እንደተዳረች... ~ከዛም ሲናፍቃት እንዴት እንደምትብሰለሰልና በመጨረሻም ስላሰለፉት ነገር ሁሉ አመሰግናው እሱም ጥሩ ትዳር እንዲገጥመው እንዴት እንደምትመኝ ይነግረናል… ~ዘፈኑን በደምብ ስትሰሙት ታሪኩ እንዲህ ነው... . . ኩኩ ሰብስቤ ~ “ወሎ”❤️ ~ኩኩ በዘፈኑ ወሎ ያደገች አንድ የልጅነት ወዳጅ የነበራት ሴት ናት....ታዲያ አሁን ሌላ ህይወት ላይ ብትሆንም ድንገት የልጅነት ወዳጇ ትዝ ብሏታል ፣ የተሯሯጡበት ሜዳና የተራጩበት ምንጭ ውሃ ሳይቀር በሀሳቧ መጥቷልና ለልጅነት ወዳጇ እንዲህ ስትል ሰላምታ ትልካለች..... “በተሯራጥንበት በሰፊው መስካችን በተራጨንበት በምንጩ ውሃችን እንዴት ነህ ልበልህ አንተ የወሎ ልጅ በልጅነት እድሜ የሆንከኝ ወዳጅ" . . . ~ታዲያ ኩኩ ለልጀነት ወዳጇ ሲያድጉ ጎረቤት ወይም ካንድ ሰፈርና ካንድ አካባቢ መሆናቸውን ታስታውሰዋለች....ይሁን እንጂ ቢሯሯጡ ፣ ቢጫወቱና ቢታገሉም ጨዋታቸው ከከንፈር ወዳጅነት እንዳላለፈ ትነግረዋለች...ግን ደግሞ አሁን ድረስ እንደምታስታውሰውም ሳትደብቅ በታችኛው ስንኝ እንዲህ ትለዋለች... "ካንድ አምባ ተፈጥረን አድገን ባንድ ሰፈር ጨዋታችን ሁሉ መች ያልፋል ከከንፈር ጨዋታችን ሁሉ መች ያልፋል ከከንፈር" . . . ~አሁን ላይ የልጅነት ወዳጇም በምን አይነት ሁኔታ እንዳለ ስለማታውቅም እንዲህ ትጠይቀዋለች... “ኧረ እንዴት ነህ እንዴት ነህ እንዴት ነህ?” . . . ~ታዲያ ትዝ ሲላት እሱ ለማማር ለመዋብ ጋቢ ማሰራት ኩታ ማስፈተል እንደማይጠበቅበት...በወሎው በባህሉ ልብስ በጉራራ ጊታ እንደሚያምርበት... ከዛም አልፎ በአልባሳቱ በባህሉ ልብስ ሲዋብ ግርማ ሞገሱ እንደሚጨምር….እጀ ጠባብ ለብሶ ጃኖ ከደረበው ጋር ሲወዳደር እሱ ሞገሱ ተፈጥሮው እንደሚበልጥ አስታውሳ እንዲህ ትለወላች... “አታሰራ ጋቢ አታስፈትል ኩታ ትዋብበታል በጉራሯ ጊታ እጀ ጠባባ ልብሶ ጃኖ ከደረበው ይምጣልኝ ያንተ አካል የተከናነበው” . . . ~ከታች ባለው ስንኝ ይሄ የከንፈር ወዳጇ እሷ ለሌላ ተድራ ወይም ባል ካገባች በኋላ እሷ ባለችበት መጥቶ እንደማያውቅና ለአይኗ እንደተራበችው እንዲህም ትላለች... “የፍቅር አስተማሪ የከንፈር ወዳጄ ባል ጋገባው ወዲያ አትመጣም ደጄ ባል ጋገባው ወዲያ አትመጣም ደጄ” . . . ~አንድም ቀን ከተደራች በኋላ በደጇ እሷ ባለችበት የማይመጣው በደህናው መሆኑን ለማወቅ ፈልጋ እንዲህ ትጠይቀዋለች... “ኧረ እንዴት ነህ እንዴት ነህ እንዴት ነህ? ኧረ እንዴት ነህ እንዴት ነህ እንዴት ነህ?” . . . ~ለሌላ መዳሯ እውነት የሆነው ይች አፍቃሪ የሰርጓ ቀን ቢሆን የልጅነት ወዳጇ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አቅፏና ስሞ እንዲለያትም ትፈልጋለች....ከዛም በኋላ በአመቱ ከባሏ ጋር ዘመድ ለመጠየቅ ወደ አደገችበት ሰፈር ስትመልስ የልጅነት ፍቅሯ ትዝ ብሏት ሆዷ እንደሚባባ ቀደማ አውቃዋለች …እሱን ማሰቧ እንደማይቀርና እንደማትረሳው ትነገረዋለች.... “ሲድሩኝ በጓሮ በድብቅ ስመህኝ ትመለስ የለም ወይ ለባል ሸልመህኝ ዘመድ ለመጠየቅ ስመጣ በአመቱ አይቀርም በፍቅር ሆዴ መባባቱ” . . . ~ጀግና ጎበዝ ቆራጥ የነበረው ወንድ ለእሷ ሲሆን እንደማይችልና እንስፍስፍ እንደሆነ አንጀት በግልፅ ትነገረዋለች.. “ከሽርጥህ መሀል ጊሌህን ሰክተህ ስፍስፍ ያልከው ለኔ ጀግንነትክን ትተህ ኧረ እንዴት ነህ እንዴት ነህ እንዴት ነህ? ኧረ እንዴት ነህ እንዴት ነህ እንዴት ነህ?” . . . ~ከእሷ ውጭ ሌላ አስቦ የማያውቀው የልጅነት ጓደኛዋ ከከንፈር ወዳጅነት ውጭ ሌላ ሳያስብ ክብሯንና ገላዋን የጠበቀላት ወዳጇን... ዛሬ እሷ ሌላ ስታገባ...የወደፊት የእሱ እጣፈንታው ከእሷ ውጭ የማያውቀው እሱ ምን ይገጥመው ?…ማንንና ምን አይነት ሴት ያገባ ይሆን ? ብላ ማሰቧን መጨነቋንም እንዲህ ስትል ከታች እንረዳለን.... “ይመጣል ፊቴ ላይ የጥንት ሁኔታህ ትዳርህ ማን ትሆን ያንተስ አለኝታህ በልጅነት ጊዜ ከኔ የታፈቀርከው ገላዬን ባደራ ይዘህ የጠበከው” . . . ~ታዲያ ይሄን መልካም የልጅነት ወደጇን ጥሩ ሚስት እንዲገጥመው ከልቧ እንዲህ እያለች ትመኝለታለች... “እህል ውሃ ባላት ኑሮን ባወቀችው ይከፍልህ ብድሩን በተጠበቀችው ይካስህ ፈጣሪ ኑሮን ባወቀችው ኧረ እንዴት ነህ እንዴት ነህ እንዴት ነህ? ኧረ እንዴት ነህ እንዴት ነህ እንዴት ነህ?” . . . ~እሷንም ካገባች በኋላ መጥቶ እንማያያት …እሱ ሆኖ ሳለ አብሮ አደግ ወዳጇ በቤተሰብ ተድራ ከሌላ ሰፈር የሚመጣው ባሏ አቅፎ እንደሚወስዳትና...የእሷና የእሱ ግንኙነት እዚህ ላይ ሊቋረጥ እንደሆነ ገብቷት እንዲህ ትላለች... “ከተዳርኩኝ ወዲያ መጥተህ ላታየኝ ላጨኝ ሰጥተህኝ ነው የምትለየኝ ሳለህ አብሮ አደጌ ካንድ ወንዝ የምንጠጣው ይወስደኛል አቅፎ ከማዶ ሚመጣው . . . “የፍቅሬ መድመቂያ ባትሆንም ቀለሜ መቼም ወንድሜ ነህ እስከ ዘላለሜ መቼም ወንድሜ ነህ እስከ ዘላለሜ” ~ታዲያ ፈጣሪ ፈቅዶ አንድ ላይ ትዳር ባንቀለስ አብረን መሆን ወይም መጋባት ባንቺል እንኳን...አንተ ለኔ ለዛላለም መልካም ወንድሜ ነህ ትለዋለች ስንብት በሚመስል ሁኔታ.... ግጥምና ዜማ ~የህዝብ አጃቢ ~ኤክስፕርስ ባንድ ✍️ Jah Mc #jahmc1 #kukusebsebe #ethiopianmusic #ethiopian_tik_tok #music @gigi_shebabaw fans

About