@diva_flawles0: #TikTo #makeup #foryoupage #fypシ #viral

diva_flawless
diva_flawless
Open In TikTok:
Region: US
Monday 24 August 2026 15:41:41 GMT
302856
6368
46
202

Music

Download

Comments

bonnatmuia8
⚠️⚡A. S. I. H. K.⚡⚠️ :
diva flawless
2026-08-27 18:10:00
1
omar_bhai.1
! O V i T o🤐 :
সব দেখসি
2026-08-30 13:47:24
1
pavan.thankam
T.PAVAN :
❤️❤️❤️beautiful
2026-08-24 16:39:23
2
fatimaking515
👑 Queen 👑❣️ :
🥰PUBG wala ❤️come 😄 only
2026-08-30 11:57:22
0
ousman4544
ousman :
hello how are you doing today wish you good health and happiness and great great success in your life and long life ❤️thank have a excellent life ❤️you really look so cute thank again
2026-08-25 16:02:00
1
nandranthulsie285
nandran :
hi sweetness 😘
2026-08-25 19:40:30
1
zaibmakinzaibzaib
❤️❤️♥️ :
hello
2026-08-29 07:18:31
0
zaibmakinzaibzaib
❤️❤️♥️ :
hii
2026-08-25 20:21:35
1
user3165949216356
خليل خالد :
قلبك قلبك قلبك قلبك قلبك قلبك قلبك قلبك قلبك قلبك قلبك قلبك قلبك قلبك قلبك قلبك قلبك قلبك قلبك قلبك قلبك قلبك قلبك قلبك قلبك قلبك قلبك قلبك قلبك قلبك قلبك
2026-08-24 21:43:35
1
jafeerhusian
Tᴄ-KᴜʀᴀᴍA 🇱🇰🛫🇰🇷 :
2026-08-29 19:35:03
0
mahin42052
Mahin420 :
😂😂😂
2026-08-29 18:33:54
0
md.pish6
MD Pish. :
🥰🥰🥰
2026-08-28 08:39:00
0
sad.boy98116
Life 🧬 is happy 😁 :
😂😂😂
2026-08-29 11:38:55
0
amoorealaamireh
amoorealaamire :
😍😍😍
2026-08-28 13:38:54
0
sk.monirul77
Sk Monirul 💝 :
😳😳😳
2026-08-29 06:46:42
0
freefireoneak1
Arsalan khan :
❤️❤️❤️
2026-08-29 20:41:01
0
amritkoirala8
amritkoirala8 :
😍😍😍
2026-08-28 10:21:17
0
aqib.jutt.aqib.al
AQIB ❤️ JUTT ❤️❤️ :
😁😁😁
2026-08-30 11:12:23
0
uasmanali995
uasmanali995🇵🇰🇵🇰804 :
❤️❤️❤️
2026-08-27 16:29:09
0
m.bilal.109
M B K 109 :
👍👍👍
2026-08-24 15:46:55
0
To see more videos from user @diva_flawles0, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

ጸሐፊ፡ አፈንዲ ሙተቂ ------- ልዑል ራስ ተፈሪ መኮንን (የኋለኛው ቀዳማዊ ኃይለ ስላሤ) ከልደቱ እስከ ሞቱ ድረስ ያለው የህይወት ታሪኩ በአግራሞት የተመላ ነው። በርካታ ጸሓፊዎች በታሪኩ ላይ ይወዛገቡበታል። አንዳንዶች ምንም ማስረጃ የሌላቸውን ጭብጦች ከርሱ ጋር ለማያያዝ ይሞክራሉ። የርሱን ታሪክ ለመቅበር እና ስብእናውንም ለማዋረድ ይሞክራሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ እርሱ የሰራቸውን ክፉ ድርጊቶች እየዘለሉ ደግ ደጉን ብቻ ያወሩለታል። ከዚህ ፈቅ የሚሉት ኢትዮጵያ በረጅም ክፍለ ዘመናት ያበቀለችው “ሙሉእ በኩለሄ” የሆነ ብቸኛ ንጉሧ ተፈሪ መኮንን እንደሆነ ይሰብካሉ። አልፎ ተርፎም “በሰው አምሳል የተፈጠረ አምላክ ነው” በማለት እርሱን የሚያመልኩ ወገኖች አሉ።         በዚህች አጭር ሐተታ የተፈሪ መኮንንን ሙሉ የህይወት ታሪክ ይቅርና የሩቡን ሩብ እንኳ ላወጋችሁ እንደማልችል ይታወቀኛል። ሆኖም በሀረር ከተማና በሌሎችም የምስራቅ ኢትዮጵያ አካባቢዎች በተፈሪ መኮንን ዙሪያ የሚነገሩ አፈ-ታሪኮችንና በሰነድ የተመዘገቡ እውነተኛ ወሬዎችን በጥቂቱ ላጋራችሁ እችላለሁ።    *****  *****  *****    በተፈሪ ላይ ከሚነገሩት አፈ-ታሪኮች መካከል አንዱ ልደቱን የሚመለከተው ነው። ልጅ ተፈሪ ብስል ቀይና መልከ መልካም ከመሆኑም በላይ ከአባቱ ከራስ መኮንን ወልደ ሚካኤል ጋር የመልክ መመሳሰል አይታይበትም። በዚህም የተነሳ የህንዳዊው ሙሐመድ ዓሊ ልጅ መሆኑ እስከ አሁን ድረስ ይነገራል። በርካታ ማሕበረሰቦች አፈ-ታሪኩን ለማስረገጥ እንደ ማስረጃ የሚመዙት ልደቱ የተፈጸመበትን ስፍራ ነው።  ተፈሪ መኮንን ሀምሌ 16 ቀን 1884 ዓ.ል. ኤጀርሳ ጎሮ በተባለችው አነስተኛ ከተማ (ከሀረር በስተሰሜን ምስራቅ 45 ኪ.ሜ ያህል ራቅ ብላ የምትገኝ) ነው የተወለደው። ልዑል ራስ መኮንን በዘመኑ የሀረርጌ ገዥ የነበሩ ሲሆን ተቀማጭነታቸውም በሀረር ከተማ ነው። ታዲያ “የራስ መኮንን መቀመጫ በሀረር ከተማ ሆኖ እያለ ልጅ ተፈሪ ኤጄርሳ ጎሮ የተወለደው በምን ምክንያት ነው?” የሚል ጥያቄ ሲቀርብ በታሪክ ጸሐፊያን የሚሰጠው ምላሽ “ራስ መኮንን ሀገር ለማረጋጋት ወደ ጃርሶ ወረዳ (ኤጀርሳ ጎሮ) ተጉዘው እያለ ከርሳቸው ጋር የነበረችው ባለቤታቸው ምጥ ያዛትና ተፈሪን እዚያ ወለደችው” የሚል ነው።   አንዳንድ የአፈ-ታሪክ ምንጮች እንደሚሉት ግን ተፈሪ በኤጀርሳ ጎሮ የተወለደው እናቱ (ወ/ሮ የሺ እመቤት ዓሊ) ከራስ መኮንን ጥቃት ለማምለጥ ከጃርሶ ኦሮሞዎች ዘንድ በጥገኝነት ገብታ በነበረበት ጊዜ ነው። እነዚሁ ምንጮች እንደሚሉት የተፈሪ እናት የራስ መኮንን ወዳጅ ከነበረው ህንዳዊው ሙሐመድ ዓሊ ጋር ድብቅ ግንኙነት ነበራት። ከዚህም ግንኙነት ልጅ ተፈሪ መኮንን ተጸነሰ። እያደር ሆዷ እየገፋ ሲመጣ ግን መሸበር ጀመረች። “ራስ መኮንን ከነቃብኝ ያጠፋኛል” ብላ ስለገመተችም ቅሌን ጨርቄን ሳትል ብንን ብላ ጠፍታ ወደ ጃርሶ ኦሮሞ የጎሳ መሪዎች ኮበለለች። ነፍሷንና ልጇንም ከራስ መኮንን ጥቃት እንዲታደጓቸው ተማጸነች። “ሞጋፈቻ” በሚባለው ባህላዊው የኦሮሞ ህዝብ ደንብ መሰረትም የጎሳው አባል ሆነች። የጎሳው መሪዎች ጉዳዩን ከራስ መኮንን ጋር በእርቅ እስኪጨርሱት ድረስም እዚያው መኖሩን መረጠች። ሽምግልናው ከመገባደዱ በፊት ምጥ ስለመጣባት አንድዬና ብቸኛ ልጇን እዚያው ተገላገለች።      ራስ መኮንን በሚስታቸው ሁኔታ በእጅጉ ቢናደዱም ሽማግሌዎች ላቀረቡት ማግባቢያ እሺታቸውን ገለጹ። ሚስታቸውም ከኤጀርሳ ጎሮ ተመልሳ ወደ ቤታቸው እንድትገባ ፈቀዱላት። ህጻኑንም ልጅ እንደ ልጃቸው ተቀብለው ማሳደግ ጀመሩ። እያደር በልጁ ላይ በሚያዩት ለየት ያለ ብሩህነት እጅግ መመሰጥ ጀመሩ። በመሆኑም “ይህ ልጅ እኔን ይተካል” የሚል ትንቢት ተናገሩ። በዚህም የተነሳ ሀገሬው በሙሉ ልጁን በአትኩሮት ማየት ጀመረ።  *****  *****  *****   ይህ በዝርዝር ያወጋኋችሁ ታሪክ በሰነድ አይታወቅም። ሆኖም “ተፈሪ የሙሐመድ ዓሊ ልጅ ነው” የሚለው አጽመ-ታሪክ ተፈሪ በህይወት እያለ እንኳ በሹክሹክታ ይነገር እንደነበር በርካታ ምንጮች ይጠቁማሉ። በጣሊያን ወረራ ዘመን ደግሞ አንድ ግለሰብ ተፈሪ የሙሐመድ ዓሊ ልጅ ነው የሚል ሐተታ በጋዜጣ ጽፎ ነበር። ይሁንና ሐተታው በዘመኑ ምሁራን ብዙም አልተዘመረለትም። ይብስ ብሎም በወቅቱ ለጣሊያኖች በባንዳነት አድረው “የቄሳር መንግሥት መልዕክተኛ” የተሰኘው ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ለመሆን ከበቁት ነጋድራስ አፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ ከፍተኛ ተቃውሞ ነው የቀረበበት። ነጋድራስ አፈወርቅ “ወይ አብዶ ወይ ሰክሮ ካልሆነ በስተቀር ማን ነው ተፈሪ የመኮንን ልጅ መሆኑን የሚክደው?” በማለት ጸሐፊውን እንደዘለፉት የያኔውን ኩነት በቅርበት የታዘቡት አምባሳደር ብርሃኑ ድንቄ “ቄሳርና አብዮት” በሚለው መጽሐፋቸው ገልጸዋል።  እኔ የዚህ መጣጥፍ ጸሓፊም “ተፈሪ የራስ መኮንን ልጅ ናቸው” ከሚሉት ወገኖች ጋር እስማማለሁ፡፡ ህንዳዊው መሐመድ ዓሊ ጸጉሩ ሉጫ ከመሆኑ ውጪ ከተፈሪ ጋር የመልክ መመሳሰል የለውም፡፡ በሌላ በኩል ሙሐመድ ዓሊ የሀረር ነዋሪ የሆነው ልጅ ተፈሪ ከተወለደ ከዓመታት በኋላ ነው፡፡ ደግሞም የልጅ ተፈሪ እናት ወይዘሮ የሺእመቤት ዓሊ በጣም መልከ መልካም እንደነበረችና ተፈሪም እርሷን እንደሚመስል ሶስት የሀረሪ ሽማግሌዎች አጫውተውኛል፡፡ ሌሎች ምንጮችም ይህንን ይመሰክራሉ። ስለዚህ ራስ ተፈሪ በሰራቸው በርካታ ጥፋቶች ባልወደውም የራስ መኮንን ልጅ በመሆኑ ላይ ጥርጣሬ የለኝም፡፡ -------- ተፈሪ መኮንን መጀመሪያ ላይ ለጋብቻ ያጫት ሴት “አስቴር” የምትባል የእቴጌ ጣይቱ ዘመድ ነበረች፡፡ ነገር ግን አቤቶ እያሱ (ልጅ እያሱ) ስልጣን ሲይዝ ልጅ ተፈሪ በብርቱ ሊቀናቀነው እንደሚችል ገመተ። በመሆኑም በዲፕሎማሲያዊ ጋብቻ ሊሸብበው ወሰነ። በዚህም መሰረት ተፈሪ “አስቴር”ን ትቶ የእህቱ (የወይዘሮ ስሒን ሚካኤል) ልጅ የነበረችውን መነን አስፋውን እንዲያገባ ጠየቀው፡፡ ተፈሪም ጋብቻውን ተቀበለ። ይህ በሚወሰንበት ወቅት ወይዘሮ መነን ራስ ልዑል ሰገድ ከሚባል ባላባት ጋር በሞቀ ትዳር ላይ ነበረች። ብዙ ልጆችም ነበራት።   የጋብቻው ዕለት ሲደርስ ወይዘሮ መነንን ለመውሰድ አራት ሺህ የደጃ/ች ተፈሪ አጃቢ ከሀረር ወደ አዲስ አበባ ተልኮ ነበር። ታዲያ የተፈሪ አጃቢዎች አዲስ አበባ ደርሰው ወ/ሮ መነንን ከትዳራቸው እስኪነጥሉ ድረስ እርሷም ሆነች ባለቤቷ ራስ ልዑል ሰገድ በተፈሪና በእያሱ መካከል ስለተደረገው ስምምነት አንድም መረጃ ያልነበራቸው መሆኑ ነው። ------- አፈንዲ ሙተቂ ሰኔ 11/2005 ዓ.ል. ተጻፈ። ሀረር- ምስራቅ ኢትዮጵያ

About