@nhungchanreview: nó rẻ mà nó đẹp #kedungmypham #kedanang #kedungdodanang #giadungtienich #goclamdep

Nhung Chan
Nhung Chan
Open In TikTok:
Region: VN
Thursday 10 September 2026 08:44:00 GMT
1347
4
0
0

Music

Download

Comments

There are no more comments for this video.
To see more videos from user @nhungchanreview, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

ክረምቱን በናዝሬት 🫠 ✍️ክረምቱ ሲመጣና የሰማዩ ደመና አዳማን ሲያቀዘቅዛት፣ ከተማዋ ሌላ የተለየ ውበትና ድባብ ትለብሳለች። በተለይ በምሽት ለሚደረግ የእግር ጉዞ (Night Walk) ከአዳማ ጎዳናዎች የተሻለ ምን ቦታ አለ? ​አዳማን ዝም ብሎ በቃላት መግለጽ ከባድ ነው። ከተማዋን ለሚያውቃት ሰው አዳማ ማለት መጠሪያ ብቻ አይደለችም፤ በውስጧ የኖረ፣ አየሯን የተነፈሰ እና የህዝቧን እንግዶችን ተቀባይነት የቀመሰ ሰው መቼም የማይረሳት የህይወት ትልቅ ምዕራፍ እንጂ! ​ ያ የማይጠገበው የናፍቆት አየር እና ድባብ ከአዲስ አበባ ተነስተው ፈጣኑን መንገድ ይዘው ወይንም በድሮው መንገድ በደብረዘይት አድርገው ወደ አዳማ ሲገቡ መጀመሪያ የሚቀበልዎት ያ ለስላሳውና ሞቅ ያለው የከተማዋ ንፋስ ነው። አዳማ የሙቀት ከተማ ናት ይባላል፤ ግን የክረምቱ አየር የከተማዋን ሙቀት ለስለስ ሲያደርገው፣ ያ ንፋስ የሚከብድ ሳይሆን ልብን የሚያሞቅ፣ ሰውን ወደ ውጭ ወጥቶ እንዲንቀሳቀስ፣ እንዲዝናና እና ህይወትን እንዲያጣጥም የሚያደርግ ልዩ ማግኔት ይኖረዋል😍 ✨ውድ ቤተሰቦቼ  አዳማ ካፈራቻቸው የ 90ዎቹ ሙዚቀኞች መካከል በቁጥር አንድ ደረጃ የሚጠቀሰው እሱ ነው። በተለይ በ 90ዎቹ ምርጥ ምርጥ ስራዎቹን አስደምጦናል።
ክረምቱን በናዝሬት 🫠 ✍️ክረምቱ ሲመጣና የሰማዩ ደመና አዳማን ሲያቀዘቅዛት፣ ከተማዋ ሌላ የተለየ ውበትና ድባብ ትለብሳለች። በተለይ በምሽት ለሚደረግ የእግር ጉዞ (Night Walk) ከአዳማ ጎዳናዎች የተሻለ ምን ቦታ አለ? ​አዳማን ዝም ብሎ በቃላት መግለጽ ከባድ ነው። ከተማዋን ለሚያውቃት ሰው አዳማ ማለት መጠሪያ ብቻ አይደለችም፤ በውስጧ የኖረ፣ አየሯን የተነፈሰ እና የህዝቧን እንግዶችን ተቀባይነት የቀመሰ ሰው መቼም የማይረሳት የህይወት ትልቅ ምዕራፍ እንጂ! ​ ያ የማይጠገበው የናፍቆት አየር እና ድባብ ከአዲስ አበባ ተነስተው ፈጣኑን መንገድ ይዘው ወይንም በድሮው መንገድ በደብረዘይት አድርገው ወደ አዳማ ሲገቡ መጀመሪያ የሚቀበልዎት ያ ለስላሳውና ሞቅ ያለው የከተማዋ ንፋስ ነው። አዳማ የሙቀት ከተማ ናት ይባላል፤ ግን የክረምቱ አየር የከተማዋን ሙቀት ለስለስ ሲያደርገው፣ ያ ንፋስ የሚከብድ ሳይሆን ልብን የሚያሞቅ፣ ሰውን ወደ ውጭ ወጥቶ እንዲንቀሳቀስ፣ እንዲዝናና እና ህይወትን እንዲያጣጥም የሚያደርግ ልዩ ማግኔት ይኖረዋል😍 ✨ውድ ቤተሰቦቼ አዳማ ካፈራቻቸው የ 90ዎቹ ሙዚቀኞች መካከል በቁጥር አንድ ደረጃ የሚጠቀሰው እሱ ነው። በተለይ በ 90ዎቹ ምርጥ ምርጥ ስራዎቹን አስደምጦናል። "ክረምቱን በናዝሬት.." እና "ዲምቢ.." እሱ የሚታወቅባቸው ስራዎቹ ናቸው። ግን የችሎታውን ያህል ብዙ ስራዎችን አልሰራም። ታለንቱን አልተጠቀመበትም። በጣም ታለንትድ ልጅ ነው። ነገር ግን የብቃቱን ያህል ብዙ ሙዚቃዎችን አልሰራም። አሱ በዘመናችን ካሉ ስመጥር ድምፃዊያን እና ዜማ ደራሲያን ዉስጥ አንዱ ነዉ! በአንድ ቀን ብቻ ብዙ ግጥምና ዜማዎችን መስራት ይችላል። ፈጣን ነው። በድምፃዊነት ቢሆን ከቀናት በፊት ያደረሰንን "ጊዜ አይሄድም" ጨምሮ ለህዝብ ያደረሳቸው እዮሪካ እና ኦሜርታ የተሰኙ 3 አልበሞች አሉት ስራዎቹም በመላው ኢትዮያውያን ዘንድ እውቅና እና አድናቆትን ያተረፉለት ሲሆን ከነእሱም በተጨማሪ “የትዝታው ፈረስ”፣ “ አይመሬት ያለ ሰው” “ሸገር ሸገር” እና “ይቅርታን” የመሳሰሉ ተወዳጅ ነጠላ ዜማዎችን ሰርቶ ለአድናቂዎቹ አበርክቷል። የዛሬው ተመስጋኝ ባለታሪካችን የ90ዎቹ ፈርጥ ተወዳጁ የዜማ እና ግጥም ደራሲ ድምፃዊ አህመድ ተሾመ (ዲምቢ)🙌 ታዲያ ዛሬ የጋበዝኳቹ ሙዚቃን አካቶ ባልተወራት ድንቅ አቀናባሪው ጅግሳ ታደሰ ተሰናድቶ ለህዝብ የደረሰው የአህመድ ተሾመ ከአልበምም በላይ ትዝታን በውስጡ አጭቋል 11 ሙዚቃዎችን ያካተተው ይህ "እዮሪካ" አልበም አውራአምባን እና ፅጌሬዳ አይነት እጅግ ውብ ሙዚቃዎችም አይረሱም👌 "ክረምቱን በናዝሬት በአዳማ ከተማ ምሽት ለእግር ጉዞ የምትወጣው ቀድማ በፍቅረኞች መንገድ ነበር የማገኛት ያኔ ለህረፍት በክረምቱ ነው ብዬ ዘግይታ ስንቱን ቀን ጠበኳት ብረዱኝ ችዬ በምሽቱ"… በልጅነታችን በአፍላ አይምሮ "ዲንቢ ለዲንቢን" በክረምቱ ስንጫወት ጨዋታው ያሰባስበናል በዝናብ በካፍያው እየተመታን ሳንጠለል ከጓደኞቻችን ጋር ሆነን የማይረሳ ትዝታን ዘርተናል፡፡ ዛሬ አሰብ አረግንና ልጅነታችንን እና አህመድ ተሾመ (ዲንቢ)ን ፍለጋ ተጠያቂ ናዝሬት ብለህን በፍቅር ጣታችንን ስንጠቁም እሱም በሶስተኛ አልበሙ ተከሰተ እውነትም "ጊዜ አይሄድም" ሲል መጥቷል፡፡ የጉብዝናን ጥንካሬ የካበ የብዙ ጊዜ ቆይታውን ለበጎ መሆኑን የነገረን ነው ማለት ይቻላል፡፡ 📍 እስቲ እሱ በግጥም እና ዜማ የተሳተፈባቸው በርካታ ስራዎችም ያሉት ቢሆንም እንደዉ ከብዙ በጥቂቱ ላስታውሳቹ ለማዲንጎ አፈወርቅ - ላላተርፍ፣ ለፀሀዬ ዮዋሐንስ - ማን ልበልሽ፣ ለአሊ ቢራ እና ሄለን በርሄ - ሲያዳ፣ ለብዙዓየሁ ደምሴ - የህልሜ ንግስት፣ ለፀደንያ ገ/ማርቆስ እና ቤቲ ጂ - ጀግኒት፣ ለሀይማኖት ግርማ - ከዚራ 2፣ ለሚኪያስ ቸርነት - ግርማ ሞገሴ፣ ለዘቢባ ግርማ - ገራገር፣ ለሀመልማል አባተ እና ሜላት መንገሻ - ሀ ሴት፣ ለታረቀኝ ሙሉ - እንደዋዛ እና ስሚያቸው፣ ለመሳይ ተፈራ - ይሰማል እና ፋሽን፣ ለታደለ ሮባ - ሳሮን ገላ እና መውደድን ለኢሳያስ ታምራት - እያዳነ ያማል፣ ለደማላሽ ንጉሴ፦ አደይ ሎጋ፣ የተሰኙትን ዜማዎች ማንሳት ይቻላል . . . አህመድ ልፍትህ አብቅቶ እንኳን ለ3ኛ አልበምህ በቃህ እያልኩኝ መልካም እድል በመመኘት ለዛሬ አበቃሁ እናመሰግናለን🙏🙏 🗣️ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን🫡 Musictube #fyp #አህመድተሾመ #ክረምቱንበናዝሬት #ethiopianmusic #musictube369

About