@zyjddv: #Meme #MemeCut

zyjddv
zyjddv
Open In TikTok:
Region: US
Friday 30 October 2026 14:12:55 GMT
249
0
0
0

Music

Download

Comments

There are no more comments for this video.
To see more videos from user @zyjddv, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

ሞት ይብቃን ! ሙቶች እንዴት ናችሁ እኛ ደኅና ነን ፣ ከቤተስኪያን ጓሮ ሰው ዘርተን ከረምን ፣ ከቤተስኪያን ጓሮ ሰው እየዘራችሁ ፣ ሲበሰብስ እንጂ ሲበቅል አላያችሁ ፤ ረገጡኝ ብለህ ምድር አትቆጣ ፣ ይህ ሁሉ ያንተ ነው ልብሱን ቢያነጣጣ ፤ ረገጥኩሽ ምድር መልሼ መልሼ ፣ እከፍለው የለ ወይ መላ አካሌን ክሼ ፣ እነርሱ እየሄዱ እየሸኘናቸው ፣  እንዴት ይታዘቡን የምንቀር መስሎአቸው ፤ በሉ እናንተ ሂዱ እኛም ወደዚያው ነው ፣ ድሮም መንገደኛ ፊትና ኋላ ነው ።              ና ምነው ፣ ና ምነው !!! የሞቱት የሞቱ አይደሉም ፣ ዝም ቢሉም በሕሊናችን እየተጫወቱ ነው ። ለጆሮ መናገር አቁመው ለልባችን እየተናገሩ ነው ። የምንቀር መስሎን የገፋናቸው ፣ ይደላን መስሎን እንጀራ የነጠቅናቸው ፣ ያንዱ ላንዱ ይሆን መስሎን ስማቸውን ያጠለሸናቸው በውስጣችን ያጫውቱናል ። ሞታቸው ሞታችንን ያሳስባል ። እነርሱ ሲሞቱ ሁሉም ነገር ምቹ የሚሆን መስሎን ነበረ ። መከራው ለቋሚው ይብሳል ። የሞተው አንድ ጊዜ ሲሞት ገዳይ ግን ዘጠኝ ጊዜ ይሞታል ፣ ሞትን ተመኝቶ ያጣታል ። ፍርደ ገምድል ዳኛ ቢለቀው ደም ያሳድደዋል ። የወኅኒው ደጃፍ ቢከፈትለት የሕሊና እስር ቤት ሥራውን ይጀምራል ። ነጻነት የውስጥ መለቀቅ ነው ፣ ይህም የሚገኘው ለእውነትና ለቅንነት በመኖር ነው ። ሟችስ ይሙት ገዳይ መግደል አይሰለቸውም ወይ  እስኪባል በምድሪቱ ላይ ደም ይፈሳል ። አገሩ ላይ ሁኖ አገሩ የሚናፍቀው ወገን በእንባ ይርሳል ። የሞቱት ዐረፉ እኛ ግን እየተናወጥን ነው ። እነርሱንስ እኛ ቀበርን እኛን የሚቀብር ማን ይሆን ? የሚል ጥርጣሬ እየወዘወዘን ነው ። አዎ ሙታን እንዴት ናችሁ  እኛ እያነቡ እስክስታ አድክሞናል ። በአንድ ዓይን እያለቀሱ በአንድ ዓይን መሳቅ አስክሮናል ። ሙታን እንዴት ናችሁ ? ስለ ስሙ የተገደላችሁ ፣ ያንን ዋጋ ከፋይ ጌታ አገኛችሁት  እናንተስ አምናችሁ ሞታችሁ ፣ እኛ ክደን እንዳንኖር እንፈራለን ። ለሃይማኖት መሞት ሳይሆን መኖር አቅቶናል ። የእናንተ መከራ ለሰዓታት ነው ፣ የገዳያችሁ ስቃይ ግን ለዘመናት ነው ። ግድያ ምን ስም ይሰጠው ፣ በሕግ ወንጀል ፣ በባሕል ነውር ፣ በሃይማኖት ኃጢአት ነው ። ትክክለኛ ገዳይ ፣ ትክክለኛ ሟች የለም ። የሕይወት ባለቤት እግዚአብሔር ነው ።  ዝማሬዎቻችን ማደንዘዣ ፣ ስብከቶቻችን ማፍዘዣ እንዳይሆኑ ማሰብ ያስፈልገናል ። እየሞትን “አለን…ሁሉን አልፈን” እያልን መዘመር ፣ “ሲገድሉን እንበዛለን” እያልን በመቀነሳችን ላይ ካፌዝን ተገቢ አይደለም ። በዚህ ዘመን ላይ ሰው ስለ እምነቱ መሞት አይገባውም የሚል የአሳብ ልዕልናን መያዝ አለብን ። እግዚአብሔር ፈቅዶ ስለ ሰጠው ማንነቱ ሰው የሞት ዕጩ መሆን አይገባውም ። ይህ ሥልጣኔን ፣ ሰውነትንና ሃይማኖትን የሚጋፋ ነው ። ያልተወለደ ፣ የዜግነት ድርሻ የሌለው ንብረት ማፍራት ይችላል እያልን ዜጋው መኖሪያ ካጣ ያልሠራነው ብዙ ሥራ እንዳለ ማሳያ ነው ። ስለ ሞቱት ሰማዕታት ብለን ዘምረናል ። በሞታቸው ላይ ሌላ ሞት እየመጣ እንጂ ሞታቸው ሲያፈራ እያየን አይደለም ። ሀገረ እግዚአብሔር በተባለች ምድር ላይ ካህን በመንበሩ ላይ ሲገደል እንደ መስማት የሚያስፈራ ነገር የለም ። የአንድም ሐዋርያ ደም ባልፈሰሰባት ምድር ላይ የክርስቲያን ደም ዕለታዊ ግብር ሲሆንባት ሊቆጨን ይገባል ። አብርሃም ሊንከን፡- “በሌላው ሰው ጀርባ ላይ ጅራፍ ሲያርፍ ለማይሰማው ሰው አዝንለታለሁ ብሏል ። ከሞቱት በላይ የሚያሳዝን ሰው በሌላው መከራ ስሜት አልባ የሚሆን ሰው ነው ። ግድያ እንደ ወረርሽኝ ነው ፣ ጥበትም ማለቂያ የለውም ። ዳር የሚሰማው ችግር አንድ ቀን ቸልተኛው በር ላይ ይቆማል ። አለሁ እያሉ ተበልተው ያለቁትን ፣ የክርስቲያን አገር የነበሩትን ማሰብ አስፈላጊ ነው ። የጥንትዋ ኑቢያ ፣ ግብጽ ፣ ቱኒዝያ ፣ ሊቢያ ፣ አልጀርስ የክርስቲያን መዲና ፣ የቀኖናት መፍለቂያ ፣ የሊቃውንት መገኛ ፣ የክርስትና ዋልታ ነበሩ ። እንደ ጋንግሪን እያደገ መጥቶ ጥፋት ጨረሳቸው ። ኢትዮጵያ ከእነዚያ እንደ አንዱ የማትሆንበት ምንም ምክንያት የለም ።  ኢትዮጵያ የምትድነው እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ስትዘረጋ ብቻ ነው ። ዛሬ እጆችዋን የዘረጋችው ወደ ኃያላን አገራት ነው ። የተረከብናት ይህች የከበረች ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን አደጋ ላይ ናት ። ከውጭ አደጋ በላይ በውስጥዋ ያለው መከፋፈልና የእረኛና የመንጋ ረሀብ ሊጎዳት ተቃርቧል ። እረኛም መንጋም እንዳታጣ ትልቅ ስጋት ውስጥ ገብታለች ። ይህ ቀን እንደሚመጣ የተናገሩና ያሳሰቡ አባቶች ነበሩ ፣ ሁሉም ተገፍተው አልፈዋል ። እነርሱ ዐርፈዋል እኛ እየተወዘወዝን ነው ። ያመንኩትን አውቀዋለሁ የሚል አማኝ የለንም ። በእኛ እውቀት ዐርፎ ፣ በበዓላት ድምቀት ተስቦ የሚመጣ አማኝ እያበዛን ነው ። ወጣቱን የት ነህ ? ብለን አልፈለግነውም ፣ ሲመጣም አዋክበው የሚያስወጡ አጋፋሪዎችን አቁመናል ። እንኳን የካደውን ልናሳምን ያመነውንም ለማስካድ ዳር አድርሰነዋል ። ቤተ ክርስቲያኑን ሳይጠላ እኛን እየጠላ የራቀን ብዙ ነው ። የእኛ መልከ ጥፉነት የቤተ ክርስቲያንን ውበት ሸፈነው ። ቤተ ክርስቲያን ትልቅ የምጥ ዘመን ላይ ናት ። ለማልቀስም ቀኑ የረዳን አይመስልም ። “ጦጣ ታስራ ትዘፍናለች” እንዲሉ ሆታችንና እልልታችን ቀኑን ያየ አይደለም ።  ሁላችንም እንሞታለን ፣ ታሪክን ፣ ሃይማኖትን ፣ ባሕልን ፣ ቅንነትን ፣ አንድነትን ገድለን መሞት ግን የሞት ድራቢ ነው ። የፍቅር ተቃራኒው ጥላቻ ይመስለናል ፣ የፍቅር ተቃራኒው ግን ግዴለሽነት ነው ። በአካል ከሚሞቱት በላይ ርኅራኄ በእኛ ልብ ውስጥ ሲሞት ዘላለማዊ ሞት ነው ። ራስን በሌላው ሰው ቦታ አድርጎ አለማስቀመጥ ከሰውነት ማኅበር በፈቃደኝነት መልቀቅ ነው ። ምድሪቱ ሟች ጠግባለች ፣ የሚሞተው ሰው ይብቃ !  ለፈጠርከው የምትራራ ና ምነው ፣ ና ምነው !!! ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ.ም.      $&

About