@ky837: #CapCut

Kiki🎀
Kiki🎀
Open In TikTok:
Region: ID
Tuesday 17 November 2026 11:31:11 GMT
194
35
1
0

Music

Download

Comments

h3n.pr
penggilakopi :
🥰🥰🥰
2026-11-17 18:44:29
0
To see more videos from user @ky837, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

)
)"የዛሬ 50 ዓመት ገደማ የመጀመሪያ የሥራ ቦታዬ በጎጃም እምብርት በምትገኘው ፍኖተ ሰላም ነበር። በወቅቱም አብዛኛውን ጊዜ ብቸኛው ሐኪም እኔ ነበርኩ። ከዚያ ዘመን የማልረሳው ትልቁ ትዝታዬ ግን እኔ ሐኪም ሆኜ ሳለ እኔን ያከሙኝና ኢትዮጵያዊነትና አማራነት ምን እንደሆነ ያስተማሩኝ የዳሞት ገበሬዎች ናቸው። አማርኛቸው፣ ልበ ሙሉነታቸው፣ ደግነታቸው፣ ሳቃቸውና ትዕግሥታቸው ለዘላለም የማልረሳው ትምህርት ሆኖኛል። በዚያን ዘመን ጎጃም ባላባትና ጭሰኛ የሚባል ልዩነት የሌለባት፣ ሁሉም በክብር የሚኖርባት አካባቢ ነበረች። ሁሉም የተሟላ ኑሮ ነበራቸው፤ ደጋሽነታቸውም የማይረሳ ነበር። «በሞቴ ይብሉ» የሚሉት አነጋገር እስከዛሬ ከአእምሮዬ አይጠፋም። በወቅቱ የሚጠጡት ውኃ ኮረፌ ነበር፤ ለሕፃንም ለአዋቂም የዕለት መጠጥ ይህ ነበር። አብዛኛው ገበሬም ጫማ አያደርግም ነበር። የእግራቸው ጥንካሬ ይገርመኝ ነበር፤ እኔም ለመሞከር ብሞክር አልቻልኩም። ጥርሳቸውን ባይቦርሹም ከሕፃን እስከ ሽማግሌ ጥርሳቸው ጤናማና ሙሉ ነበር። የአፍ ሽታም ሆነ የሰውነት ጠረን አያስታውሳቸውም። በቀን ሁለት መለኪያ ሴስቴ መጠጣትም የጎጃም ሰዎች የተለመደ ልማድ ነበር። እኔ ግን ለመላመድ አልቻልኩም። አንድ ቀን ገበያ ላይ ያላወቀኝ ገበሬ ሴስቴ ሊጋብዘኝ ሲል አልስማማም አልኩት። እሱም በሳቅ «እንደኛ ደመ መራራ ስላልሆኑ ነው» ብሎ መለሰልኝ። የወቅቱን የፖለቲካ ሁኔታን በማስታወስ፣ አብዮት የተባለው እንቅስቃሴ ጎጃምን አልዘለቀም፤ ካድሬዎችም ከከተማ ወጥተው ወደ ገጠሩ መሄድ ይቸገሩ ነበር። ለስብሰባ ሲጠሩም ሰው አይመጣላቸውም ነበር። ጎጃም ራሷን የቻለች ሪፐብሊክ እስከመሆን የደረሰች ትመስል ነበር። የአካባቢው ባላባቶች ፊታውራሪና ደጃዝማች በሚል የክብር ማዕረግ ይጠሩ ነበር። እኔም የትውልድ ሐረጌን ካጣሩ በኋላ በየድግሳቸው የክብር እንግዳ አድርገው ይጋብዙኝ ነበር። ከእነርሱ ጋር በክብር ማዕድ እቀርብ ነበር። በዚያን ዘመን ፍኖተ ሰላም አንድ በሬ አራጅ ብቻ ነበራት። በሬ ማረድ እንደ ዝቅተኛ ሥራ ይቆጠር ስለነበር ይህ ሰው የሚበላው ሥጋ ብቻ ነበር። ብርንዶ መውደዴን ካወቀ በኋላ ግን ጥሩ ሰንጋ ባገኘ ቁጥር በሌሊት ወደ ግቢዬ ይመጣና በሩን አንኳክቶ፣ «ይሄውልህ አንተ ጅብ፣ ዛሬ ቀንቶሃል፤ ሽንጡ ያንተ ነው» ይለኝ ነበር። ሥጋውን ሸጦ ከጨረሰ በኋላ ሽንጡን ይዞልኝ ይመጣል። ከጎረቤት ጠጅ በማንቆርቆሪያ ይመጣል። ሽንጡን በግቢዬ ውስጥ ባለው ዛፍ ላይ ሰቅለን በጆፌና በመንደር ውሾች ተከበን እንበላ ነበር። ከዚያም ለእሱ የገዛሁለትን የደገላ ምንጣፍ አንጥፎ እዚያው ያድራል። አካባቢው ጅብ የሚበዛበት ቢሆንም እንዳይበላው ብዬ ወደ ቤት ገብቶ እንዲተኛ ስነግረው፣ «ጅቡ ይፈራኛል» ብሎ ይመልስልኝ ነበር። በእርግጥም ጅቦች መጥተው አጠገቡ ያለውን ቅሪት እንጂ እሱን ምንም አያደርጉትም ነበር። ታዲያ ዳሞትና ጎጃም እንዴት ከልቤ ሊጠፉ ይችላሉ? #Gojjam

About